www.maledatimes.com በሚኒሶታ-ሚድዌስት የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የኮቪድ-19 የድጋፍ አሰባሰብ ወቅታዊ ሪፖርት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በሚኒሶታ-ሚድዌስት የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የኮቪድ-19 የድጋፍ አሰባሰብ ወቅታዊ ሪፖርት

By   /   April 17, 2020  /   Comments Off on በሚኒሶታ-ሚድዌስት የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የኮቪድ-19 የድጋፍ አሰባሰብ ወቅታዊ ሪፖርት

    Print       Email
2 0
Read Time:2 Minute, 56 Second

በሚኒሶታ-ሚድዌስት የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት የኮቪድ-19 የድጋፍ አሰባሰብ ወቅታዊ ሪፖርት

መግቢያ
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከልና ቫይረሱ በአገራችን የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቋቋም አቅጣጫ መውረዱ ይታወሳል። በሚድዌስት ከሚገኙ የተለያዩ ከዳያስፖራ አደረጃጀቶች ጋር ቴሌ-ኮንፈረንሶችን በማካሄድ ኮሚቴ በማደራጀት በአገሩ አሰራር GoFundMe ሂሳብ በመክፈት፣ የህክምና ቁሳቁሶችን በኢትዮዽያ አየር መንገድ እንዲጓጓዝ ዋሽንግተን ዲሲ ወደ ሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ ትዕዛዙ እንዲደርስ በማድረግና በየስቴቱ የተዋቀረው ኮሚቴ ገንዘብ በመሰብሰብና በማስተባበር ወደ አገር ቤት ገንዘቡ እንዲላክ በማድረግ ላይ እንገኛለን።
በአገራችን ያለውን የኮረና (ኮቪድ-19) ስርጭት በአገራችን ለመግታት በአገራችን ከተቋቋመው ግብረ-ሀይል የወረደውን እቅድ መሠረት በማድረግ ሪፖርት መላካችን ይታወሳል። ካለፈው ሪፖርት በተጨማሪ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ በሚኒሶታ -ሚድዌስት የኢፌዲሪ ቆንስላ ጽ/ቤት የተከናወኑ ስራዎችና ከኢትዮጵያዊያንና ተውልደ ኢትዮጵያዊያን የዳያስፖራ አደረጃጀቶች እንዲሁም የተለያዩ ማህበራት የተሰበሰበውን የገንዘብ ድጋፍ ወቅታዊ አፈጻጸም እንደሚከጸለ ሪፖርት ቀርቧል።
የህዝብ ግኑኝነት 

• በቆንስላ ጽ/ቤቱ የሶሻል ሚዲያ፣ ከሚኒሶታ በሚተላለፈው በኦሮምኛና በአማርኛ ኤፍ ኤም ሬድዮ ( KFAI ሬድዮ) በዘሐበሻ፣ ኦቢኤን፣ በኦኤምኤን እና ኦዲኤን እንዲሁም በኢሊኖይስ ስቴት ቺካጎ ከተማ፣ በአይዋ ስቴት ዲሞይን ከተማ፣ በሳውዝ ዳኮታ ስቴትሲፎልስ ከተማ በኔብራስካ ስቴት ኦማሃ ከተማ፣ በሚዙሪ ስትት በሴንትሊዊስ ከተማ፣ በኬንሳስ ስቴት በሚዙሪ-ኬንሳስ ከተማ፣ በዊስኮንስን ሰቴት ከሚገኙ የኢትጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የኮሚኒቲ አደረጃጀቶችና የተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር በቴሌ ኮንፈረንስ ውይይቶችን በማድረግ ላይ እንገኛለን:: በጤና ባለሙያዎች የተደገፋ የተለያዩ መልዕክቶችን በመቅረፅ በተደራጁ “በዋትስአፕና በፌስቡክ “ ቡድን በመጠቀም የግንዛቤ ማስጫበጫና የመረጃ ልውውጥ እንቅስቀሴዎች በስፋት እየተካሄደ ይገኛል።
• በሳውዝ ዳኮታ ስቴት በሲፎልስ ከተማ የሚገኘው የእንስሳት ስጋ ማዘጋጃና ማቀነባበሪያ ድርጅት (Smithfield Foods Plant) ካምፓኒ ከሚሰሩ 3000 ሰራተኞች መካከል 1500 የሚሆኑት ኢትዮጵዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊን ይገኙበታል፡፡ አፕሪል 14 ቀን 2020 በካምፓኒው ሠራተኞች ላይ በተደረገው የቫይረሱ ምርመራ እስካሁን ከ600 በላይ ሠራተኞች በቫይረሱ የተያዙ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በሲፎልስ ከሚገኙ የኢትዮጵያዊንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የኮሚዩኒቲ አደረጃጀቶች፣ የሐይማኖት ተቋማትና እድሮች ባገኘነው መረጃ መሠረት በቫይረሱ ከተያዙት 600 ሠረተኞች ከ50 በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን መረዳት ተችሏል። እነዚህም ታማሚዎች በስቴቱ በሚገኙ ሆስፒታሎች ውስጥ ተኝተው ለመታከም የሚረዳ በቂ ቦታ ባለመኖሩ በየቤታቸው እራሳቸውን በማግለል ተቀምጠዋል፡፡ በቋንቋ ሊግባቡ ከሚችሏቸው ዶክተሮች እና የህክምና ባለምያዎች ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡ ሆኖም ግን እንዚህ በየቤታቸው ያሉት ሰዎች ቫይረሱን ወደ ቤተሰቦቻቸው የማስተላለፍ እድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ስጋት አለ። የቫይረሱን ሰርጭትና ተጽኖ ለመቀነስ እንዲረዳ የቆንስላ ጽ/ቤታችን በአካባቢው ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ዶክተሮች፣ የኮሚዩኒቲ አደረጃጀቶች፣ እድሮችና የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ጋር በመመካከር ብዛት ያላቸው የኮሚዩኒቲ አባላት የተሳተፉበት በቴሌ ኮንፈረንስ በባለሙያ የታገዘ ትምህርታዊ መግለጫ እንዲሰጥ ማድረግ ተችሏል። ይህም ትምህርታዊ መግለጫ ጠቃሚ መሆኑ በመታመኑ በየሳምንቱ እንዲሰጥ ከስምምነት ተደርሷል፡፡
የገንዘብ አሰባሰብ

በዚህ ሀገር ህግ ከህዝብ ገንዘብ መሰሰብ ለጽ/ቤታችን የማይቻል በመሆኑም በየኮሚዩኒቲ አደረጃጀቶች ባሉ መዋቅሮች በመጠቀም ገንዘቡን እንዲያሰባስቡና ከኛጋር መረጃ በመለዋወጥ አገር ቤት ለዚህ ዓላማ በተከፈቱ የባንክ አካውንቶች፣ እንዲሁም በኢትዮ-ቴሌኮም በተከፈው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ድህረ-ገጽ እንዲሁም በ(Go Fund Me) ቦመጠቀም እንዲሰባሰብ ከስምምነት የደረስን ሲሆን እስካሁን የተሰበሰበው ገንዘብና ምንጩ ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርቧል፡፡

የገንዘቡ ምንጭ በዶላር (USD)በብር

1. Friendly Home Health Care and Axis Family Clinic $ 38,000(1,300,000)
2.በአይዋ የኢትዮጵያ ተወላጆች $ 2,500
(85,000)
3.በሲፎልስ ኢትዮጵያ ተወላጆች $ 5,150
(175,000)
4.Chiro Charity Group $ 22,650(770,00 Birr)
5.International Oromo Health Professionals Association $67,965(2,310,810 birr)
6.ሲኮመንዶ ኮሙኒት-ሰምንት ሺህ ዶላር የሚያወጣ የሴኒታይዘር ኬሚካልና ማቀላቀያ መሳሪያው $8,000(272,000 Birr)
7.ዲጂታል ቴርሞሜትር (10) $1,000
(34,000 Birr)

Total $145,265 (4,939,010 Birr)

• የቆንስላ ጽ/ቤታችን እስካሁን ከኮሚኒዩቲ አደረጃጀቶች የሐይማኖት ተቋማት፣ የተለያዩ ማህበራትና እድሮች የቦርድ አመራርና አባላቶቻቸው ጋር በመተባበር የድጋፍ ማሰባሰቡን ሥራ የቀጠለ ሲሆን የአደረጃጀቶቹ አመራሮችም ገንዘቡ ለታለመለት ዓላማ ማለትም በአገር ቤት በሽታው ቢስፋፋ አቅም ለሌላቸው የምግብ መገዣነት ፣ ቫይረሱን ለመከላከል ለሚረዱ የተለያዩ የመከላከያ ቁሳቁሶችና የህክምና ሙያተኞች የመከላከያ ቁሳቁሶች መግዣ መዋል እንሚገባው አሳስበዋል፡፡ እኛም ከኮሚዩኒቲ አደረጃጀቶች ጋር በየጊዜው የምናደርገው የቴሌ ኮንፈረንስ ፕሮግራም አጠናክረን በመቀጠል የሚሰባሰቡ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፎችን እየተከታተልን ሪፖርት የምንለክ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

​​​ከሰላምታ ጋር
​​​​​​​​እውነቱ ብ.ደበላ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar