www.maledatimes.com ፈጣሪ ያጣመረው እውነተኛ ትዳርን ኮሮና አለየውም…. - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

ፈጣሪ ያጣመረው እውነተኛ ትዳርን ኮሮና አለየውም….

By   /   April 17, 2020  /   Comments Off on ፈጣሪ ያጣመረው እውነተኛ ትዳርን ኮሮና አለየውም….

    Print       Email
1 0
Read Time:1 Minute, 50 Second

የሰባ እንድ አመቱ ጣሊያናዊው ጂያንካርሎ እና የሰባ ሶስት አመቷ ባለቤታቸው ሳንድራ በትዳር አለም ከተጣመሩ ግማሽ ምእት አለም አስቆጥረዋል፣በእነዚህ ወርቃማ የትዳር ዘመናቸው ሁሌም የትዳር ቋንቋቸው በፍቅር የተሞላ ነው።

ታዲያ እነዚያ ለበርካታ የዚህ ዘመን ወንደላጤዎች፣ ሴት ላጤዎች እና ባለትዳሮችም የመልካም ትዳር ተምሳሌት ሊሆኑ የሚችሉት ሁለቱ ጣሊያናዊያን ጥንዶች ሰሞኑን አለምን ባስጨነቀው፣ለጊዜው መድሀኒት ባልተገኘለት በቀሳፊው የኮሮና ቫይረስ፣ሳምባ ቆልፍ ወረርሺኝ ተጠቅተው ፌርሞ ማንቺ በተባለው ከተማ በሚገኘው ሞሪይ ሆስፒታል ውስጥ ጎን ለጎን አልጋ ለመያዝ ተገደዋል።

እንደ ደይሊ ሜል ጋዜጣ ሰሞነኛ ዘገባ ላለፉት ሀምሳ አመታት በፍቅር አለም ውስጥ የተጓዙት ሁለቱ የእድሜ እና የትዳር ጠገብ ባለትዳሮች ሰሞኑን በሆስፒታል አልጋቸው ላይ ሆነው የአየር መተንፈሻ(ቬንትሌተር) ተገጥሞላቸው ሳሉ ሁለትን ጥንዶችን በቅርበት የምትንከባከብ ፌሪቴ የተባለች የህክምና ባለሙያ የሁለቱ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እና እድሜ ጠገብ ጥንዶች ልዩ የትዳር ፍቅርን ከመታዘቧ በተጨማሪ ከተጣመሩ ሀምሳ አመት መሆኑን ትረዳለች።

የህክምና ባለሙያዋም ፊሬቲ በዚህ ብዙዎች አንገታቸውን በደፉበት ፣የኮሮና ወረርሺኝ እጅግ የሚዋደዱትን በሚነጥቅበት አሳዛኝ ወቅት በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ ሁለት አልጋ ላይ እገዛ በማግኘት ላይ ያሉት ሁለት ጥንዶችን ለማስደስት በመወጠን ኬክ፣ በሆስፒታሉ ውስጥ እሳት መለኮስ ስለማይቻል(የማይበሩ ሀምሳ ሻማዎችን ) በኬኩ ላይ በመደርደር ፣ሁለቱ ጥንዶች ቪንትሌተር እገዛ ላይ በመሆናቸው አልጋቸውን ሳይለቁ፣እጆቻቸውን በማጨባበጥ በተወሰኑ የሆስፒታሉ ሰራታኞች እና በለስላሳ የፍቅር ሙዚቃ አጃቢነት ለዘመናት ሲጓጉለት የነበረው የሀምሳኛ የፍቅር እና የትዳር ዘመናቸውን ለአስር ደቂቃ ባልበለጠ ክብረ በአል አከናውነውታል።

ስለነበረው ልዩ አጋጣሚም የህክምና ባላሙያዋ ፌሬቲ ስትናገር “አልጋውን እንዳስጠጋነው ፣ ሁለቱ ገመምተኞችን እጅ ለእጅ እንዲያያያዙ ስናመቻችላቸው በውስጣቸው የነበረው የፍቅር ትኩሳትን ለመግለጽ ይከብዳል፣እኛም ሁላችንም በሁኔታቸው በ ደስታ እንባ ተራጨን ፣ነገር ግን በእንደዚህ አስጨናቂ ጊዜ እና የሞት ሸለቆ ውስጥ ይህን የመሰለ አጽናኝ እና የፍቅር መንፈስን ሞት ሞት በሚሸተው በሆስታሉ ውስጥ ለእስር ደቂቃዎች ማየት ለእኛም ልዩ ፍቅር እና ብርታትን ጭሮብናል” በማለት ደስታውን ገልጻለች።

የክፍሉ ሰራተኞች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አድርገው ሁለቱ ጥንዶች በአፋቸው ላይ የመተንፈሻ መሳሪያ(ኦክስጂን)ተገጥሞላቸው አይን ለአይን መተያየት ሳይችሉ፣ እጅ ለእጅ በመጣመር በሆስፒታሉ አልጋ ላይ የተከበረው ሀምሳ አመት የህይወት እና የፍቅር ጉዞ መታሰቢያ ምስልን የተላከላቸው የሁለቱ የኮሮና ተጠቂ ጥንዶች ልጆች በሰጡት አስተያየት “ዛሬ ከሆስፒታሉ ትልቅ ስጦታ በማግኘታችን ደስተኞች ነን።እማማ እና አባባ ከጅማሮው ለመጣመር እና ለመፈቃቀር የተፈጠሩ ፣ ዛሬ በብዙዎቻችን ዘንድ የሌለ ሁሌም ፍቅርን ልብ ለልብ የሚያጣጥሙ አዛውንቶች ናቸው።” በማለት ከአንድ መቶ ስድሳ ሽህ በላይ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ በተጠቁባት ፣ከሀያ ሺህ በላይ በሞት በተነጠቁባት ጥንታዊቷ ጣልያን ውስጥ ይህንን የመሰለ አስገራሚ ገጠመኝ በማየታቸው ሀለቱ ልጆቻቸው ሀሉን ላከናወነው ፈጣሪን በማመስገን ፣ወደር የለሽ ደስታቸውን እና ለህክምና ባላሙያዎችም ልዩ አድናቆታቸውን ገልጸዋል ።

(ታምሩ ገዳ)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
100 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar