የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅን አስመልክቶ ዘሃበሻ በዘገበው ዘገባ ላይ በስደት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር ለአየር መንገዱ ሃሳብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ የዋና ስራ አስኪያጁ ክስ ውድቅ እንዲያደርገው እና ዋና ስራ አስኪያጁ የመጡበት መንገድ እስከ መጨረሻው የማያስኬዳቸው መሆኑን አክሎ ገልጿል ። በአየር መንገዱ አመራር እና አየር መንገዱ የህዝብን ንብረት በግል በመጠቀም ያደረጉት የሙስና ወንጀል ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ሁላችንም የምንረዳው ነው ።
ለዚህም ከተለያዩ አካላት በአየር መንግዱ እንዝላል አሰራር ላይ ያቀረቡልንን መረጃዎች ከማውጣታችን በፊት እና በአለም አቀፍ የበረራ ድርጅቶች ውስጥ ያላቸውን መሪ ተዋናይነት የሚያስናክለውን ይህንን ወንጀላቸውን ከመግለስ የተቆጠበው የዘሃበሻ ሚዲያ ፣ በማለዳ ታይምስ እጅ ውስጥ የሚገኙ መረጃዎች እንዳሉ ሳንገልጽ አናልፍም ። በተለይም በአቶ ሳሙኤል የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ በጀርመን እና በጀርመኑ የኢትዮጵያ አየር መን ገድ እንዲሁም በአቶ ስዩም መስፍን እና ሌሎች ባለስልታናት የተሰራው ድብቅ ወንጀል የሁላችንንም ጆሮ የሰጠ ነው ።
ይህም ብቻ ሳይሆን ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በመስሪያቤት ውስጥ ይደርስ የነበረውን ወሲባዊ ጥቃት፣ ሙስና እና መድልዎም አስመልክቶ ሰራተኞቹ ያደረሱን መረጃዎች ጥቂቶቹ ናቸው ።
የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ስኮላር እንሰጣለን በማለት ከአዲስ አበባ ወደ ጀርመን እንዲሄዱ በማድረግ ከፍተኛ ገንዘብ የሰሩባቸው እና የጀርመን ኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳᎂል የዚሁ እጣ የደረሳቸው እና በዚሁ ስራ ከአቶ ስዩም መስፍን ፣ ወዩ ሮባ እና የአየር መንገዱ አመራር ጋር በጋራ በመሆን ከፍተኛ ምዝበራ ያደረጉ ግለሰቦች ነበሩ ።
የተለያዩ ባለሃብቶችን እንዲባረሩ እና በምትኩ እነዚህ ሰዎች በሃገሪቱ ላይ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ስራ እንዲሰሩ ከተደረጉት ሰዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ። ሌሎቹንም ስም ዝርዝር በቀጣይ ሪፖርት ማለዳ ታይምስ ይዞ ይቀርባል ።
በአየር መንገዱ ቅዋሜ ያላችሁ ሆነ በሙስና ከስራችሁ የተባረራችሁ የጾታችሁ ጥቃት የተፈጸመባችሁ ሌሎች ሰራተኞችን ጨምሮ ማናችሁም ኢትዮጵያውያኖች ያላችሁን መረጃ edito@maledatimes.com መላክ ትችላላችሁ !!
Average Rating