www.maledatimes.com የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያጋጠመውን አደጋ ለመቀነስ የተዘጋጀ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ ስራ ላይ እንዲውል ወሰነ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያጋጠመውን አደጋ ለመቀነስ የተዘጋጀ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ ስራ ላይ እንዲውል ወሰነ

By   /   April 29, 2020  /   Comments Off on የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያጋጠመውን አደጋ ለመቀነስ የተዘጋጀ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ ስራ ላይ እንዲውል ወሰነ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 59 Second

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያጋጠመውን አደጋ ለመቀነስ የተዘጋጀ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ ስራ ላይ እንዲውል ወሰነ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያጋጠመውን አደጋ ለመቀነስ የተዘጋጀ የኢኮኖሚ ማነቃቂያ ስራ ላይ እንዲውል ወሰነ

#አዲስ አበባ፣
#ሚያዝያ 20፣ 2012

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያጋጠመውን አደጋ ለመቀነስ መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች ላይ በቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ ሚያዚያ 16 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው በቫይረሱ ምክንያት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያጋጠመው አደጋ የአብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል ኑሮ የሚጎዳ መሆኑን ተመልክቷል።

ከዚህ በመነሳትም መንግስት ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፎችን እያደረገ እንደሚገኝ ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ የጠቆመው።

የዚህ ድጋፍ አካል የሆነውን የኢኮኖሚ ማነቃቂያ በማድረግ፣ ወረርሽኙ በህብረተሰቡ ጤና ላይ የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል የሚወስዳቸው እርምጃዎች ውጤታማ እንዲሆኑ፣ በተለያዩ መስኮች ተቀጥረው በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞች ከስራ እንዳይሰናበቱ የድጋፍ እርምጃ እንዲወስዱ ለማድረግ የገንዘብ ሚኒስቴር ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበ ሲሆን፥ ምክር ቤቱም በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል ስራ ላይ እንዲወል መወሰኑ ነው የተመለከተው።

በተጨማሪም የኮሮና ቫይረስ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከል መንግስት ለሚያደርገው ጥረት የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ዜጎች እንዲበረታቱ በጎ አድራጊዎች ለመንግስት የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ ግብር ከሚከፈልበት የ2012 ለግብር ክፍያ ላይ የ20 በመቶ ያልበለጠ ተቀናሽ ማድረግን፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ እና ተርን ኦቨር ታክስ የሚያስታውቁበት እና የሚከፍሉበት ጊዜ በአንድ ወር እንዲራዘም ማድረግን፣ የንግድ ድርጅቶች በስራ ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ያጋጠማቸው ኪሳራ ማሸጋገርን፣ በስራ መቀዛቀዝ ምክንያት የጡረታ መዋጮን ለመክፈል የተቸገሩ አሰሪዎች የሚቀጥሉትን ሶስት ወራት የጡረታ መዋጮ ሂሳብ ከሚጠበቅበት ከሀምሌ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እንዲከፍሉ የክፍያ ሽግሽግ ማድረግን በተመለከተ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ላይ በመወያየት ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ በገንዘብ ሚኒስቴር የቀረቡትን የተለያዩ የብድር ስምምነቶች እና የማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቷል።

ብድሮቹ ከጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ጋር የተፈረመውን ለጅማ-ጭዳ እና ሶዶ-ሳውላ የመንገድ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ፤ ከጣሊያን መንግስት ጋር የተፈረመውን የጤና ዘርፍ የልማት ግቦች ፕሮግራም ማስፈጸሚያ፤ ከጣሊያን መንግስት ጋር የተፈረመውን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ክህሎት ማሻሻያእና የስራ ፈጠራ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ፤ ከኮሪያ ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ ጋር የተፈረመውን የአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ፤ ከኮሪያ ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ ጋር የተፈረመውን ለመሬት መረጃ አስተዳደር ስርዓት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ እንዲሁም ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የከሊፋ ፈንድ ለድርጅት ልማት ጋር አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች የብድር አቅርቦት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውሉ ብድሮች ላይ ሲሆን፥ ብድሮቹ ከሀገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ፣ በረዥም ጊዜ የሚከፈሉ፣ ከ1% በታች ወለድ የሚከፈልባቸው እና ረዘም ያለ የእፎይታ ጊዜ ያላቸው መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት የብድር ስምምነቶቹ ይጸድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ተወስኗል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on April 29, 2020
  • By:
  • Last Modified: April 29, 2020 @ 9:38 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar