0
0
Read Time:40 Second
ትግራይ ከፌዴራል መንግስት ልማትና ኢንቨስትመንት እንዲሁም ከአጠቃላይ የሃገራችን የብልፅግና ጉዞ ፍፁም አትገለልም!!ነብዩ ስዑልነብዩ ስዑል
ለዛሬው እለት ከደረሱት ቱባ ዜናዎች አንዱ በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በመላው የአገራችን ክፍሎች ሊሰሩ ውል የታሰረላቸው የ11.6 ቢልዮን ብር የመንገድ ፕሮጆክቶች አንዱ በትግራይ ክልል የዛላምበሳ-ዓሊቴና-መረዋ-ዕዳጋሓሙስ የሚሰራው የ32 ኪ/ሜትር አስፋልት መንገድ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት እንዲሰራው ውል የተሰጠው ደግሞ የህወሓቱ ሱር ኮንስትራክሽን ነው።
ከዚህ በተጨማሪም በትግራይ ክልል ልዩ ስሙ ምዕራብ ትግራይ ታሕታይ አድያቦ የቆዳ ስፋቱ 198.695 ካሬ ስኩየር ሜትር በሆነ ቦታ የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ በፌዴራል መንግስት ተሰቷል።
የኢትዮጵያዊ አንድነታችንና የእኩልነታችን ምስክር የሆኑ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችም በቅርብ ይፋ ይደረጋሉ፤
በመደመር እሳቤ የትግራይ እንዲሁም የመላ አገራችን ብልፅግና እዉን ይሆናል!!
ነብዩ ስሑል ሚካኤል
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating