www.maledatimes.com ዶ/ር ቴዎድሮስ ፣የ20 ሚሊዮን ዶላሩ የጭቁኝ ተክሉ ጉዳይ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዶ/ር ቴዎድሮስ ፣የ20 ሚሊዮን ዶላሩ የጭቁኝ ተክሉ ጉዳይ

By   /   May 22, 2020  /   Comments Off on ዶ/ር ቴዎድሮስ ፣የ20 ሚሊዮን ዶላሩ የጭቁኝ ተክሉ ጉዳይ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 5 Second

የእለም የጤና ጥበቃ /WHO ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከጭቁኝ ተክል መድሃኒት ማግኘቷን ከገለጸችው ከደቡብ አፍሪካዊቷ ማዳጋስካር ጋር የሚስጥራዊነት ሰንድ ውል ለመፈራረም መወጠናቸው ተነገረ።

የማዳጋስካር ፕ/ት አንድሬይ ራጆሊና እሮብ እለት በትዊተር ገጻቸው ላይ ” ከአለም የጤና ድርጅት፣ዋና ኃላፊ ከዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ጋር በቴሌኮንፍራስ ባደረግነው ውይይት ኮቪድ ኦርጋኒክ / Covid-Organics/ የተሰኘው ከጭቁኝ ተክል የተቀመመው ንጥረ ነገር በሙከራ ደረጃ ለመጠቀም የሚደረገው ሂደትን እንደሚያግዙን ፣ጥረታችንን እንደሚያደንቁ እና የመድሃኒቱ ምስጢራዊነት/Confidentiality clause/ እንዲጠበቅ ለመፈራረም ተስማምተናል” ሲሉ በገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው በትዊተር ገጻቸው ላይ ከፕ/ት አንድሬይ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ጠቅሰው “በጋራ ጉዳይ ተባብረን ለመስራት፣አለማችንን ከወረርሽኙ ነጻ ለማድረግ ተባብረን እንደምንሰራ ተስማምተናል” በማለት አብራርተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ዶ/ር ቴዎድሮስ ወደ ማዳጋስካር የሰልክ ጥሪ ከማድረጋቸው ቀደም ብሎ ሰሞኑን በስፋት የተነገረ ነገር ቢኖር ” የማዳጋስካሩ ፕ/ት ከፈረንሳዩ ፍራንስ 24 ቴሌቭዥን ጋር በጭቁኝ ተክል መድሃኒት ዙሪይ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ባደረጉት ሰፊ ቃለምልልስ ላይ የአለም ጤና ድርጅት /WHO /ማዳጋስካር ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከጭቁኝ ተክል አገኘሁት ያለችውን መድሃኒትን ዋጋውን ለማስጣት ዶ/ር ቴዎድሮስ የሚመሩት አለማቀፉ የጤና ተቋም ለፕ/ት አንድሬይ የሀያ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሙስና ገንዘብ/ብራይብ/ በመስጠት አፍሪካዊያን ወንድሞቻቸውን ለማስገደል ተሞክሯል “የሚል ነበር።

ይህ ከመቶ ሺህ በላይ የማህበራዊ ድህረ ገጾች አልፎ፣ዪቲዩበሮች ሰሞነኛ የአለማችን ትኩስ መነጋገሪያ ርእስ የፈጠረው ደግሞ በታንዛኒያ ውስጥ የሚታተመው ታንዛኒያ ፐርስፔክቲቭ የተሰኘው ጋዜጣ እና በተለይ ሌላኛው የእናት ድርጅቱ ውጤት የሆነው ፣በስዋህሊኛ ቋንቋ የሚታተመው Fahari Yetu, የተባሉት ጋዜጦች ግንቦት/ሜይ 14 2020እኤአ በፊት ለፊት ገጻቸው ላይ መዘገባቸው ነበር። ታንዛኒያ ፐርስፔክቲቭ ጋዜጣ የሀያ ሚሊዮኑ ዶላሩን የጉቦ ሙከራጉዳይ ይጥቀስ፣ እንጂ የሴራው ጠንሳሽ ማንነትን በጋዜጣው ላይ ሆነ በማህበራዊ ገጾቹ ላይ አልገለጸም ።

ይሁን እንጂ የማዳጋስካር ፕሬዜዳንታዊ ጽ/ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ሊቫ ራማናማሮ ለፈረንሳዩ ኤኤፍ በሰጡት ምላሽ” ፕ/ት ሪቪሪያ ባደረጉት ቃለምልልስ ላይ አንዳችም ስለ ሙስና ሙከራ ያወሩበት ቦታ የለም”በማለት ዘገባውን ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል። ቀደም ባሉት ጊዜያትም አሜሪካ እና ቻይና “የማዳጋስካር የጭቁኝ ተክሉ የኮሮና ቫይረስን ለመበከል/ለመመረዝ ደጎስ ያለ ሚሊዮን ዶላሮችን ለመስጠት ተስማምተዋል” የሚል ወሬ መናፈሱን ዜና ዘገባው አውስቷል።

የአለም ጤና ተቋም ፣ ሆነ የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከል እና ቀጥጥር ተቋም (CDC)በበኩላቸው የጭቁኝ ተክል ወደ ህዝቡ ዘንድ በጸረ ኮሮና ቫይረስ መድሃኒትነት ከመሰራጨቱ በፊት ሳይንሳዊ ጥናት እና በቂ ሙከራ ሊደረግበት ይገባል በማለት የማዳጋስካር መንግስትን በተለያዩ አጋጣሚዎች አስገንዝበዋል።

ማዳጋስካር ግን ከጭቁኝ ተክል ተገኝቷል የተባለው የጸረ ኮሮና ቫይረስ መድሃኒትን የተጠቀሙ 105 ህሙማኖች በአስር ቀናት ውስጥ “መፈወሳቸውን” በመግለጽ ታንዛኒያን ጨምሮ አስር ለሚጠጉ የአፍሪካ አገራት ማሰራጨቷን ትናገራለች። የተከፈተባት አለማቀፍ የማጥላላት እና የመጠራጠር ዘመቻ ፕሬዝዳንቱ ሳይቀሩ”አፍሪካዊ አገር በመሆናችን እንጂ አንዲት አወሮፖዊት አገር ብንሆን ኖሮ ጫወታው ሌላ ነበር” በማለት ለወባ፣ለሆድ ፣ለጉንፋን እና ለኢንፌክሽን ህመሞች ፍተን መድሃኒት መሆኑ የሚታመነው የጭቁኝ ተክል ጉዳይን በቀላሉ እንደማያልፉት በአጽኖት በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

(ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

Image may contain: 1 person
Image may contain: 1 person, text
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on May 22, 2020
  • By:
  • Last Modified: May 22, 2020 @ 10:54 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar