0
0
Read Time:40 Second
**************
በአገራችን የሚታየው የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከዕለት ወደ ዕለት እያደገ በመምጣት በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለጸው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ካምፓሶቹ የፊት ጭንብል ማድረግን አስገዳጅ የሚያደርግ መመሪያ አውጥቷል።
ዩኒቨርሲቲው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ቀደም ሲል ያስተላለፋቸው መሠረታዊ የመከላከል ዘዴዎች የሆኑት እጅ መታጠብ፣ ርቀት መጠበቅ እና የፊት ጭንብል መጠቀም በመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ የሚያበረታታ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መቆዩቱን አስታውሷል።
ነገር ግን የተላለፉት የጥንቃቄ እርምጃ መመሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መላላት እየታየባቸው በመሆኑ እና የቫይረሱ ስርጭት እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቅሷል።
ይህንን ተከትሎ ከግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ማንኛውም ሰው የፊት ጭንብል ሳያደርግ ወደ ግቢ መግባት፣ በግቢ ውስጥ ያለ ጭንብል መንቀሳቀስ እና ጭንብል ሳያደርጉ በቢሮ ውስጥ ሥራ መሥራት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አስታውቋል።
የዩኒቨርሲቲው ስታንዳርድስ ሴፍቲ እና ሴኪዩሪቲ ዳይሬክተር እና የሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ሐላፊዎች መመሪያውን ተግባራዊ እንዲያደርጉም አሳስቧል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating