የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በፈቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን ገለፁ፡፡
ወይዘሮ ኬሪያ በመቐለ ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤዎች ሀላፊነታቸውን በመልቀቅ ለተተኪው አፈጉባኤ ሲያስረክቡ የቆዩት መልቀቂያቸውን ለምክር ቤቱ በማቅረብ እንደነበር ይታወቃል፡፡
ወይዘሮ ኬሪያ ሚያዚያ ወር 2010 ዓመተ ምህረት ላይ ነበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው የተመረጡት፡፡
ምክር ቤቱ 5ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን የፊታችን ረቡዕ እና ሀሙስ ለማካሄድ አባላቱን ጠርቷል፡፡ በዚህም ሁኔታ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም በገዛ ፍቃዳቸው ሰልጣናቸውን የለቀቁበት ምክንያት ብለው የተናገሩት። “ሕገ መንግሥት ከሚጥስና አምባገነናዊ አካሄድን ከሚያራምድ ቡድን ጋር” አብረው ለመስራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እንደሆነ ዛሬ በሰጡት መግለጫ መናገራቸው ተገልጿል።
በሌላም በኩል ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲ አባል አመራሮች እንደተናገሩት ከሆነ ወይዘሮ ኬርያ የመልቀቂያ ድምጻቸውን በትግራይ ቴሌቪዝን ለማቅረብ የሞከሩትም ሆነ ሃሳባቸውን ያቀረቡት ከህወሃት አባላት ከፍተኛ ግፊት እንዳለባቸው በመረዳት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በሌላም በኩል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ እንደተናገሩት ከሆነ በህወሃት ዘመነ መንግስት የተፈጸመው የህገ መንግስት ጥሰት እና የሰበአዊ መብት መገፈፍ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዝ ነው ፣ እስከአሁን ድረስ በዶክተር አብይ አስተዳደር ተፈጸመ የምንለው በቁጥር የምንመዘግባቸው የሰበአዊ ትሰቶች የሉም ፣ አሉ ቢባሉም እንኳን በአናሳ ክልሎች በተቃዋሚ አንጃዎች የሚደረጉ የህግ ጥሰቶችን አለማስከበሩ ነው ሲሉም ይጠቁማሉ ።
በሌላም መልኩ ሲናገሩ በኦሮሚያ ክልል የሰማኒያ ስድስት ሰዎችን ህልፈትን የዳረገውን ግለሰብ በህግ መጠየቅ ሲገባው አስቀምጦ መቀለቡ ፣ በዝዋይ ሰው ዘቅዝቀው ሲገሉ ዝም ማለቱ ፣ በአማራ ክልል ለጥናት የሄዱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሲገደሉ ዝም ማለቱ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዙሪያ በደቡብ ተወላጆች ላይ የተፈጸመውን ግፍ ዝም ማለቱ የህገመንግስቱን ጥሰት ያሳያል፣ ሆኖም ግን እንደ መንግስት ሆኖ ከተቀመጠበት ጊዜ ጀምሮ በመንግስት አካላቶች አንድም የተፈጸመ ሰባዊ ትሰት የለም እርሳቸው ያደረጉት የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
Average Rating