www.maledatimes.com ሐርመኒ ሆቴል ሙሉ በሙሉ ሥራ አቆመ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ሐርመኒ ሆቴል ሙሉ በሙሉ ሥራ አቆመ

By   /   June 8, 2020  /   Comments Off on ሐርመኒ ሆቴል ሙሉ በሙሉ ሥራ አቆመ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 56 Second

 

 

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገኘው እና ባለ አራት ኮከብ የሆነው ሐርመኒ ሆቴል ሙሉ በሙሉ ሥራ አቆመ። በኢትዮጵያ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ገበያ ከመቀዛቀዙ ጋር ተያይዞ ሆቴሉ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ የተገለጸ ሲሆን ከወራት በፊት በፈቃዳቸው እረፍት መውጣት የሚፈልጉትን ሠራተኞቹን ማስወጣት ጀምሮ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። የሐርመኒ ሆቴል ሥራ አስኪያጅ ዜናዊ መስፍን ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት ሆቴሉ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሥራ በማቆሙ ከቴክኒካል ሠራተኞች ውጭ ያሉ ሌሎች ሠራተኞችን በእረፍት ፍቃድ ከሥራ ውጭ ደምወዝ ተከፍሏቸው እንዲቆዩ መደረጉን ጠቁመዋል። የሆቴሉ ሥራ አስኪያጅ አንደገለጹት በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 ከተከሰተ ወዲህ የሐርመኒ ሆቴል ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ሆቴሎች የችግሩ ተጋላጭ እንደሆኑና ሥራ አቁመው እንደሚገኙ ጠቁመዋል

ዜናዊ ይህን ይበሉ እንጂ እሁድ ግንቦት 23/2012 በሆቴሉ ውስጥ ከመንግሥት ወገን ተልከናል ያሉ ግለሰቦች ከፍተኛ ፍተሻ በማድረግ ፈንጅ ማግኘታቸውን የአይን እማኞች ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።ይህን ጉዳይ በሚመለከት ዜናዊ ምንም ምላሽ እንደሌላቸው እና እውቀቱም እንደሌላቸው ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ቢንያም ብስራት የሆቴሎችን ሙሉ በሙሉ ሥራ ማቆም ተከትሎ ሠራተኞች ያለ ደመወዝ እንዳይበተኑ ለማድረግ እስካሁን ሆቴሎች ሥራ ሳይሰሩ ከኪሳቸው የኹለት ወር ደመወዝ አንደከፈሉ ገለጸዋል። ቢሆንም አንዳንድ ሆቴሎች ላይ ችግሩ ስለሚስተዋል ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ማኅበሩ እየሰራ መሆኑን ቢኒያም ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ቢኒያም ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ መከሰቱን ተከትሎ የወጣው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሠራተኞች ደመወዝ አለመክፈልን እንጂ ሥራ ማቆምና መዝጋትን አይከለክልም ብለዋል።

በሌላ በኩል ብሔራዊ ባንክ የግል እና የመንግሥት የንግድ ባንኮች ለሆቴሎች የአንድ ዓመት ብድር በአምስት በመቶ ወለድ እንደሚያቀርቡ ገልጾ ነበር። ብሔራዊ ባንክ ግንቦት 2012 ለንግድ ባንኮች በሙሉ በደብዳቤ እንዳስታወቀው፣ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ ደንበኞቻቸው ለሥራ ማስኬጃ የሚውል ገንዘብ የሚደለደለው ባንኮቹ በሰጡት የብድር መጠን እየተሰላ መሆን ይገባዋል መባሉ የሚታወስ ነው። የአዲስ አበባ ሆቴል ባለንብረቶች ማኅበር የኮሮና ቫይረስ በዘርፉ ላይ ያስከተለውን ጉዳት ለመረዳትና የመፍትሔ ሐሳብ ለመጠቆም የሚያግዝ የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ፣ አገኘሁት ባለው የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት እንደገለጸው፣ በማኅበሩ ሥር ከሚገኙ 130 ሆቴሎች መካከል 56 በመቶ ያክሉ የኮሮና ቫይረስ በፈጠረው ቀውስ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል ብሏል።

32 በመቶ የሚሆኑት አገልግሎታቸውን በከፊል ለማቆም እንደተገደዱ፣ የተቀሩት 12 በመቶ ሆቴሎች ደግሞ ከውጭ ለሚገቡ መንገደኞች በለይቶ ማቆያነት እያገለገሉ እንደሚገኙ ማኅበሩ በጥናቱ አመልክቷል። ይህን እና መሰል ጉዳቶችን ተከትሎ የሆቴል ኢንዱስትሪው በመቀዛቀዙ በማኅበሩ በኩል የብድር መክፈያ ጊዜው ለአንድ ዓመት እንዲራዘምላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውንም አዲስ ማለዳ ከዚህ ቀደም መዘገቧ ይታወሳል።

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ከተከሰተ ወዲህ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉ ላይ የበረታ መቀዛቀዝ እያጋጠመ እንደሆነ የኢፌዲሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መግለጹ የሚታወስ ነው። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ ተፅዕኖ ውስጥ የሚገኘውን የአገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ በቀጣይ ከገባበት ቀውስ ማገገም እንዲችል እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መግባቱንም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ገልጿል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar