www.maledatimes.com የቆዳ ፋብሪካዎች ከአንድ ወር በኋላ ለሠራተኞች ደሞዝ መክፈል እንደሚቸገሩ አስታወቁ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የቆዳ ፋብሪካዎች ከአንድ ወር በኋላ ለሠራተኞች ደሞዝ መክፈል እንደሚቸገሩ አስታወቁ

By   /   June 8, 2020  /   Comments Off on የቆዳ ፋብሪካዎች ከአንድ ወር በኋላ ለሠራተኞች ደሞዝ መክፈል እንደሚቸገሩ አስታወቁ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 34 Second

የቆዳ ፋብሪካዎች መንግሥት ለዘርፉ ብድር አገልግሎት ማመቻቸት ባለመቻሉ እና ለውጭ ኢንቬስተሮች (FDI) ብቻ ትኩረት በመሰጠቱ ምክንያት በኮቪድ 19 ምክንያት የተከሰተውን ችግር ተቋቁሞ መቀጠል እንደከበዳቸው እና ከወር በኋላ ደሞዝ መክፈል የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውንም አስታውቀዋል። መንግሥት ተገቢውን ያህል ለዘርፉ ትኩረት ስላልሰጠን መቀጠል የማንችልበት ደረጃ ደርሰናል ለዛውም ካሉት አብዛኞቹ የቆዳ ፋብሪካዎች ከአንድ ወር የዘለለ የሚከፍሉት ደሞዝ የላቸውም ሲሉ የቆዳ ፋብሪካዎች ማኅበር አባል ለመረጃ ማእከላት ተናገሩ። ኮቪድ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ የተለያየ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ቢያደርስም እና እያደረሰ ቢገኝም ግን ከዚህ በፊት በቆዳ ፋብሪካዎች ላይ የነበረው መቀዛቀዝ ይበልጥ ጫና ፈጥሮበት ወደ መዘጋት ሊሄድ እንደቻለ የማህበሩ ሃላፊ አስታውቀዋል።

ከዘርፉ እንድንወጣ እየተደረገ ነው የሚሉት የማህበሩ አባላት ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ሃገር ባለሃብቶች ሴክተሩ እንዳይቆዩ የሚደረጉባቸው ጉዳዮች ከቆዳ   ማስረከቡ ጀምሮ ያለው ሂደት ይጀምራል ሲሉም ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል። ቅሬታ አቅራቢው ጨምረው እንደገለጹት በቆዳ ፋብሪካ ዘርፍ ውስጥ አስከ 350 ሺህ ሰዎች በስሩ ይተዳደራሉ። በተደጋጋሚ ቅሬታ ለመንግስት ሲያቀርቡ ቢቆዩም ተገቢ የሆነ ምላሽም ሆነ ዘላቂ መፍትሔ ማግኘት ሳይችሉ እንደቀሩም ለአዲስ ማለዳ አያይዘው ገልጸዋል ።

 

የማህበሩ አባል ጨምረውም ”አንድ ድርጅት ተዘጋ (አቆመ) የሚባለው ባንክ አውጥቶ ሲሸጠው አይደለም፤ ነገር ግን መንግስት ይሄን ተረድቶ መደገፍ አልቻለም“ ብለዋል። አጠቃላይ በዚህ ዘርፍ ውስጥ ያሉት ፋብሪካዎች 30 የሚጠጉ ይሁኑ እንጂ አሁን ያሉበት ሁሉም የቆዳ ፋብሪካዎች ደረጃ ከመቀጠል ይልቅ ወደ ማቆሙ እየተንደረደሩ መሆኑም ተገልጿል። ”ለዚህም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትምነት (FDI) ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ተደርጎ ለአገር ውስጥ ባለ ሀብቶች ደግሞ ድጋፉ ቀርቶ በሀገሩ ላይ በፈለገው ዘርፍ ተሰማርቶ እንዳይሰራ የሚያደርግ የመንግስት አስተሳሰብ ነው ከዘርፉ እንድንወጣ እና እራሳችንን ችለን እንዳንንቀሳቀስ ያደረገን“ ሲሉም ጠንከር ያለ ትችት እና አስተያየት ሰንዝረዋል። ”ለመንግስት በተደጋጋሚ ይሄን ጥያቄ ብናቀርብለትም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ከቁም ነገር የሚሰማን የለም ለመድከማችን እና ወደ መዘጋት ደረጃ ለመድረሳችን ዋናው ምክንያት ይሄ ነው“ ሲሉ የማህበሩ አባል ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የዘርፉ ማኅበራት በአሁኑ ወቅት የተጋረጠበትን ከፍተኛ ተግዳሮት ለመቋቋም የብድር ሁኔታ እንዲመቻችላቸው ቢጠይቁም ከመንግሥት በኩል ይሁንታን ማግኘት እንዳልቻሉ ጠቁመዋል። ከዛም በተጨማሪ የመሃበሩ አባል እንደሚሉት ከሆነ ‹‹ ውጪ ሃገር አንዲ ኢንቨስትመንት›› ላይ ለመሰማራት ለዜጎቹ ቅድሚያ ከተሰጠ በኋላ ነው ለሌላ አገር ዜጎች ፍቃድ የሚሰጠው የሚሉት ኣባል ኢትዮጲያ ውስጥ ግን በአቅማችን ብዙ ችግር አይተን የለፋንበትን ዘርፍ ነጥቆ ለሌላ ክፍት ማድረግ ነው ቅድሚያ የሚሰጠው ብለዋል›› በዚህም ብዙ የአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብዙ መንገድ ተዘግቶባቸዋል ሲሉ የቆዳ አምራቾች ማኅበር አባል ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የኢትዮጲያ ቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢኒስቲቲውት ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ብርሃኑ ስርጃቦ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ተዘጉ እና ወደ መዘጋት ደረጃ እሄዱ ያሉ ቆዳ ፋብሪካዎች የሉም ሲሉ አስተባብለዋል ። ነገር ግን በስጋት 5 የሚሆኑ ፋብሪካዎች ተዘግተው ነበረ ቢሆንም ከመንግስት ጋር በመነጋገር ወደ ስራ እንዲመለሱ ተደርጓል ብለዋል። አለም አቀፍ ችግር በሆነው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት አብዛኛው አለም ገበያ ተዘግቷል፤ በተለይም ኢንዱስትሪ ምርቶች ወደ ውጪ ስለሆነ የሚላኩት፤ በዛም ምክንያት ወደ ውጪ የቆዳ ፋብሪካዎች ይላኩ የነበሩ ምርቶችን ባለ መላካቸው ምክንያት የመቀዛቀዝ ነገር ነው ያለው ብለዋል። በዚህም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ያለው በቆዳ ፋብሪካዎች ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞቻቸውን በፈረቃ እየገቡ እንዲያመርቱ እያደረጉ ነው እንጂ ሰራተኛ የቀነሰም የለም ሲሉ አስተባብለዋል። ከዛ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ያመርቱ ከነበረው ቀንሰውም ቢሆን በምርት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።ምናልባት የቆዳ ፋብሪካዎች ከዚህ ቀደም ይሸጡ ከነበረው እየቀነሱ ነው የሚለው ካልሆነ ኹሉም በምርት ላይ እንደሆነ ነው ተቋማችን የሚያውቀው ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።19 ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ በተለያየ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ቢያደርስም እና እያደረሰ ቢገኝም ግን ከዚህ በፊት በቆዳ ፋብሪካዎች ላይ የነበረውን መቀዛቀዝ ይበልጥ ጫና ፈጥሮበት ወደ መዘጋት ሊሄድ እንደሆነ የማኅበሩ አባላት ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar