1
0
Read Time:36 Second
ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተጎዱ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ሊደግፍ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ማስተር ካርድ ፋውዴሽን ከኢትዮጵያ ስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ፈርስት ኮንሰልት አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው የድጋፍ ፕሮግራሙን ይፋ ያደረገው። የአስቸኳይ የድጋፍ ፕሮግራሙም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑም ከማስተር ካርድ ፋውዴሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ለድጋፉም በማስተር ካርድ ፋውዴሽን አማካኝነት የ24 ነጥብ 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መነሻ ገንዘብ የቀረበ ሲሆን፥ ድጋፉም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ጠንካራ ሆነው ሰራተኞቻቸውን ይዘው እንዲቆዩ እንዲሁም ከወረርሽኙ በኋላ ፈጠራ የታከለበት የስራ እድል እንዲፈጥሩ የሚያስችል ነው ተብሏል። የገንዘብ ድጋፉ ቀላል ብድርን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች ተፈፃሚ የሚደረግ ሲሆን፥ የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ አይነት እና መጠንም እንደ ኢንተርፕራይዞቹ አቅም እና ፍላጎት የሚወሰን መሆኑም ተገልጿል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating