www.maledatimes.com ትንሽ ስለ ኤልያስ መልካ በዘለአለም ገብሬ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ትንሽ ስለ ኤልያስ መልካ በዘለአለም ገብሬ

By   /   June 17, 2020  /   Comments Off on ትንሽ ስለ ኤልያስ መልካ በዘለአለም ገብሬ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 45 Second
ትንሽ ስለ ኤልያስ መልካ
ኤልያስ መልካ በጣም ጎበዝ ከሚባሉት ሙዚቃ ተጨዋቾች ተርታ ከሚሰለፉት ውስጥ ግንባር ቀደሙን የሚይዝ ታላቅ ሰው ነው ።
ኤልያስ በብዙዎች ዘንድ ልብ ውስጥ የገባው የተለያዩ ሙዚቃዎችን በማቀናበር እንደሆነ ማንም ያውቃል፣ ከቴዲ አፍሮ ጀምሮ ፣ ሃይሌ ሩት ፣ ጆኒ ራጋ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሞኒካ ሲሳይ ታምራት ደስታ ፣ ማኪያ በሃይሉ፤ ሸዋንዳኝ ሃይሉ፣ እና ሌሎቹም ትላልቅ ቦታ የደረሱ ድምጻውያንን በተከበረ ስፍራ አስቀምጧቸዋል።
ትላንት ሰው የነበረው ኤልያስ መልካ ዛሬ በህይወት ባይኖርም (ወደ መጣህበት መሬት እስክትመለስበት ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ አፈር ነህ እና ወደ አፈርም ትመለሳለህና) በሚለው የዘ ፍጥረት ፫ ቁጥር ፲፱ ትእዛዛዊ ሃይል ወደ አምላኩ ተመልሷል። ከ40 በላይ አልበሞች ከ400 በላይ ሙዚቃዎች እንደሰራ የሚነገርለት ኤልያስ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለብዙ ዘፋኞችም ግጥምና ዜማንም ሰርቶ ሰጥቷል ፣ኤልያስ በቼሎ ብቻ ሳይሆን በፒያኖም ጎበዝ ነው። በጊታርም ጎበዝ ነው፤ ሜጀሩ ቼሎ ነው፤ ነገር ግን በአገር ባሕል የሙዚቃ መሳሪያ፣ በፒያኖ እና በጊታር ተከታታይ ትምህርቶች ነበሩት። የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ጊታሪስት የዜማ እና ግጥም ደራሲ የነበረው ኤልያስ መስከረም 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። አንድ አመት ሊሞላው የሁለት ወር ከአስራ አምስት ቀናት ጊዜ ብቻ ይቀረዋል። በሌላም በኩል በአንድ ወቅት አምላኩን በሚያመልክበት የእምነት መስመር ለብዙ ጊዜያት የእምነቱ ሃይል በመሆን ብዙ የመዝሙር ስራዎችንም ሰርቷል ፣ አገልግሏልም ። እስከ ህይወተ እልፈቱ ጊዜ ድረስ አምላኩን በማምለክ የህይወት ጥሪውን በአምላኩ ፈቃድ ወደ እርሱ እስከሚመለስ ድረስ የመጣበትን መከራ ለብቻው ሲገፋ እንደነበር ሁላችንም እናውቃለን፡፡
ኤልያስ መልካ ከሌሎች የሙያ አጋሮቹ ጋር በመሆን ለሶስት አመታት የለፋበት እና በቅርቡ ሥራ ላይ በዋለው አውታር የሙዚቃ መገበያያ ሥርዓት ሶማሊኛ እና አፋርኛን ጨምሮ በገበያው እምብዛም ቦታ ያላገኙ ማኅበረሰቦችን ሙዚቃዎች ለሽያጭ ለማብቃት ግፊት በማድረግ ላይ ነበር።
 
ድምፃውያንን ጨምሮ የሙዚቃ ባለሙያዎች ከሥራዎቻቸው ተገቢውን ጥቅም ማግኘት አለባቸው የሚል አቋም የነበረው ኤልያስ፤ ዮሐንስ በቀለ (ጆኒ ራጋ) ኃይለሚካኤል ጌትነት (ኃይሌ ሩትስ) እና ዳዊት ንጉሴ ከተባሉ የሙዚቃ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ባቋቋመው አውታር መልቲሚዲያ በኩል አውታር የተባለውን መገበያያ ሥራ ላይ አውሏል።
 
የሙዚቃ ሥራዎች ለሽያጭ ሲቀርቡ ድምፃዊ፣ የግጥም ጸሐፊ፣ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማ ደራሲ ጨምሮ ሁሉንም ባለሙያዎች እኩል ተጠቃሚ ያደርጋል ብሎ ያመነበትን የአውታር መገበያያ ሥርዓት ለማጠናከር ከባልደረቦቹ ጋር ጥረት ላይ ነበር።
 
ታዲያ ዛሬ ላይ ትላንት ስናወድሰው የነበረው ወንድማችን በህይወት በአለመኖሩ ፣ ለእኛ የአንድ ወቅት የትውስታ ጊዜያትን የምናስታውስበት ጊዜያት ሆኖብን አለፈ ፣ እርሱ ግን የዘለአለም ስራዎቹን ጥሎልን አልፏል፡፤ በአንድ ወቅት ላይ በቴሌቪዥን መታመሙን ያዩ ወጣቶች ለኤልያስ መልካ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ይሰጥ በማለት ይጮሁ ነበር እነዚያ ሰዎች ።
ኤልያስ መልካ
በአዲስ አበባ በተለምዶ አብነት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ታኅሳስ 1 ቀን 1970 ዓ.ም. የተወለደው ኤልያስ በልጅነቱ እግር ኳስ መጫወት ይወድ የነበረ ቢሆንም ወደ ሙዚቃ የማዘንበል ፍላጎት ያሳይ ነበር። ይሁነኝ ብሎ ከአስራ አንደኛ ክፍል ወደ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ከማምራቱ በፊት በቤተ ክርስቲያን ሙዚቃ ተጫውቷል።
 
በ1987 ዓ.ም. ሙዚቃን ለመማር ወደ ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በአመራበት ወቅት በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት በዋናነት ያጠናው ቼሎ ተብሎ የሚጠራውን የሙዚቃ መሳሪያ ነው። ከዚያ ባሻገር ክራር እና ፒያኖ ተምሯል። ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ከተመረቀ በኋላ በያኔው መዲና ባንድ ለሶስት አመታት ጊታር ተጫውቷል። የዛሬው ዋናው የዚህ ጽሁፍ ዋና አላማ ይህንን ሰው እንዴት እናስታውሰው የሚል አላማ የያዘ ነው ።
የዚህን ሁሉ የሙያ ባለቤት ዛሬ ማን ያስታውሰዋል? ይህ የእኔ ጥያቄ ነው ። ታዲያ
ጊዜያዊ ስሜት ይነዳቸው የነበሩ ዜጎች ፤ ዛሬ እርሱ አልፎ ፣ቤተሰቦቹ በምን ደረጃ ላይ እንኳን እንዳሉ የሚያስታውሰን የለም ፣ የእርሱ የሙት እለት መቼ እለት እንደነበር እንኳን ማሰብ አልቻሉም ። ይህ ወቅትን እየጠበቀ የሚንበለበል እሳተ ነበልባል የሆነ ስሜታችንን ታቅበን ምን አለበት የኤልያስ መልካን አንድ ነገር ትሪቡት ብንሰራ ። እባካችሁ በኪነ ጥበቡም ውስጥ በሚዲያም በኢንቨስትመንትም ሆነ በሌላም መንገድ ያላችሁ ኢትዮጵያኖች ለዚህ አንድዬ ሰው አንድ ስም ማስጠሪያ የሚሆን ነገር በጋራ አስተባብረን ብንሰራ ምን ይመስላችኋል። እንደ ሃሳብ ይንሸራሸር እና ውሳኔ ከመጣ በጋራ መተባበር ብዙ ነገር መለወጥ እንችላለን ። 
አመሰግናለሁ ።
ነፍስህን ይማረው ወዳጄ ኤልያስ መልካ
ዘለአለም ገብሬ !! Image may contain: 1 person, playing a musical instrument

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar