በሃጫሉን ግድያ አስመልክቶ በሃገራችን ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ አካባቢ በግፍ የተገደሉትን ንጹሃንን በማሰብ እና ለተደረገው የዘር ማጥፋት ወንጀልን በመቃወም እና ፍትህን ለማግኘት ያስችል ዘንድ ኢትዮጵያውያኖች በእንግሊዝ አደባባይ መውጣታቸው ተገልጿል።
በዛሬው እለት ከማለዳው ጀምሮ ሲተም የነበሩት ኢትዮጵያውያኖች አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ባንዲራ በማውለብለብ የህዝባቸው የሃገራቸው አለኝታ የሆነውን አርማ ይዘው መንቀሳቀሳቸውን ገልጸዋል።
ይህም ሆኖ ሳለ በአሁን ሰአት የሃጫሉ መገደል የሁሉንም ስሜት የጎዳ ቢሆንም በሃጫሉ መገደል ምክንያት የሌሎች ዘር ያላቸውን በሙሉ መግደል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው ገዳዮች በዘር ማጥፋት ወንጀል መከሰስ ይገባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ዶክተር አብይ ለሰላማዊ ህይወት በሚል ትእግስት እያደረገ በአሁን ሰአት ግን ይህ ትእግስት ለከት ያጣ በመሆኑ ነው የኦሮሞ ጽንፈና ቡድኖች በሃገራችን ህዝቦች ላይ የግድያ ወንጀል የፈጸሙት ሲሉ በለንደን የሚገኙ ኢትጵያውያን የገለጹት ።
በሌላም በኩል የዜጎችን ሃብት ንብረት ማውደም ፣ የሃገሪቱን ብቻ ሳይሆን የአካባቢውን የእድገት ጉዞ ወደ ኋላ መጎተት ነው ያሉት አንድ ግለሰብ በአሁን ሰአት ላይ የስራ አጥ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ ገልጸዋል፡፤ በዋሽንግተን ዲሲም በተመሳሳይ ሁኔታ የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ መደረጉንም መረጃው ያመለክታል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating