www.maledatimes.com የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ያደረጉትን የችሎት ስራ ሃምሌ 13 ቀን ይጀምራሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ያደረጉትን የችሎት ስራ ሃምሌ 13 ቀን ይጀምራሉ

By   /   July 18, 2020  /   Comments Off on የፌደራል ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ ያደረጉትን የችሎት ስራ ሃምሌ 13 ቀን ይጀምራሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 15 Second

the federal high court

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከመጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል ዝግ ያደረጉትን የችሎት ስራ ከሃምሌ 13 ቀን ጀምሮ በየደረጃው መደበኛ ችሎት ሊጀምሩ ነው፡፡

በዚህም ከሃምሌ 13 እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረሰ በሁሉም ፍርድ ቤቶች የመልስ መልስ፣ አስተያየቶች፣ የትዕዛዝ ውጤቶችን ለመቀበል የተቀጠሩ እንዲሁም እልባት ለመስጠት ጥቂት ሂደት የቀራቸው ጉዳዮች እና እስረኛ ያላቸው መዛግብት በየቀጠሮ ቀናቸው የማስተናገድ ስራ እንደሚሰራ የፌደራል ፍርድ ቤቶች ቃለ አቀባይ እና የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ነዋይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን የሚታዩ ጉዳዮች አስቸኳይነት በዳኛው፣ በፍርድ ቤቱ እንዲሁም በየደረጃው በሚገኝ አመራር አሳማኝነቱ ካልታመነበት ለቀጣዩ አመት የሚቀጠር ይሆናል፡፡

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ከሚገኙ ባለጉዳዮች የሚቀርቡ አቤቱታዎች ይስተናገዳሉም ብለዋል፡፡

በአንጻሩ ከክልል የሚመጡ የሰበር ጉዳዮች የኮቪድ19 ወረርሽኝን መከላከል ሲባል ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ የስራ አቅጣጫ በሚሰጥበት ጊዜ ወደፊት እንደሚስተናገዱም አውስተዋል፡፡

በሁሉም ደረጃ ያሉ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶች ኪቪድ19ኝን ለመከላከል የወጣውን ደንብ ተከትለው እንደሚሰጡም ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ማንኛውም ተገልጋይ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ካላደረገ ወደ ግቢ መግባት አይፈቀድለትም፡፡

ፍርድ ቤቱም ለአገልግሎቱ በቂ የንጽህና መጠበቂያ ግብአቶችን በማሟላት አገልግሎት እንደሚሰጥም አስረድተዋል፡፡

በተጨማሪም ፍርድ ቤቶቹ አዳዲስ መዝገቦችን ማለትም የቀጥታ ክስ፣ ይግባኝ እና አፈጻጸም መዝገቦችን ደግሞ ከነሐሴ 1 ቀን እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ማየት ይጀምራሉ፡፡

ነሐሴ ወር የዳኞች የእረፍት ጊዜ የነበረ ቢሆንም ያሉትን በርካታ መዛግብት ክምችትና ጫናዎችን ለመቀነስ የነሐሴን ወር የሚሰሩ ሲሆን መስከረም ወር 2013 ዓ.ም የዳኞች የእረፍት ጊዜ ይሆናል፡፡

በተረኛ ችሎት ሲስተናገዱ የነበሩ ጉዳዮችም በተረኛ ችሎት እንደሚቀጥሉም ተገልጿል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 4 years ago on July 18, 2020
  • By:
  • Last Modified: July 18, 2020 @ 3:16 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar