www.maledatimes.com የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰማንያ ሰባተኛው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰማንያ ሰባተኛው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

By   /   July 19, 2020  /   Comments Off on የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሰማንያ ሰባተኛው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 34 Second

በዚህም መሠረት፡-

  1. ም/ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በገንዘብ ሚኒስቴር የቀረቡትን የተለያዩ የብድር ስምምነቶች የማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡ ሁለቱ የብድር ስምምነቶች የተደረጉጉት ከኮሪያ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ጋር ሲሆን አላማቸውም ለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ የበጀት ድጋፍ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ እና ለኮሮና ቫይረስ (COVID-19) የሕክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት ማስፈጸሚያ የሚውሉ ናቸው፡፡ ሶስተኛው የብድር ስምምነት ከዳንስኬ ባንክ ኤ.ስ ጋር የተደረገ ሲሆን ለአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ነው፡፡ ሶስቱም የብድር ስምምነቶች አነስተኛ ወለድ የሚታሰብባቸው (ከ1% በታች)፤ የረጅም ጊዜ እፎይታ ያላቸው እና በ40 ዓመታት ተከፍለው የሚጠናቀቁ በመሆኑ ከአገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ ይጸድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡
  2. በመቀጠልም ምክር ቤቱ የተወያየው የስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ሀገራዊና አካባቢያዊ ሰላም፣ ደህንነትና ጸጥታ፣ ብሄራዊ መግባባት፣ በሀገረ-መንግስት እና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲሁም የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ፣ ቀጠናዊ ትስስር እና ትብብር ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ማድረግ፤ በተጨማሪም ቁልፍ በሆኑ ፖሊሲዎች ላይ ጥናቶች በማካሄድ ምክረ ሃሳብ ማቅረብ፣ ስትራተጂያዊ እና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ትንተና መስጠትና ለውሳኔ የሚረዱ የቅድሚያ ግምቶች ማሳየት፣ የዳታ ክምችትና የእውቀት ቋቶችን ማደራጀት ከኢንስቲትዩቱ የሚጠበቁ ተግባራት ናቸው፡፡ ም/ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል ተቀብሎ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡
  3. በሌላ በኩል የኢንቨስትመንት ረቂቅ ደንብ ም/ቤቱ የተመለከተው ጉዳይ ነው፡፡ በቅርቡ ከጸደቀውን የኢንቨስትመንት አዋጅ በአግባቡ ለማስፈጸም ይቻል ዘንድ እንደዚሁም በአጠቃላይ የኢንቨስትመንት ህግ ማዕቀፉ በኢኮኖሚው ዘርፍ እየተካሄዱ ካሉ ለውጦች ጋር እንዲናበብ ማድረግ፣ የአገር ውስጥ እና የውጭ ባለሀብቶች በግሉ ዘርፍ ሊሳተፉ የሚችሉባቸውን የኢንቨስትመንት ሥራዎች በመከለስ የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚ ውስጥ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ፤ በሥራ ፈጠራን ለማበረታታት እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና በክህሎት ሽግግር ላይ ያለውን ሚና ማሳደግ፣ በተለያዩ ሕጎች ውስጥ ተበታትነው የሚገኙትን የመንግስት አገልግሎቶች በመሰብሰብ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት፣ የኢንቨስትመንት አስተዳደር እና ቁጥጥር ሥርዓቱን ማዘመን፣ የኢንቨስትመንት ማነቆ ለሆኑ ጉዳዮች መፍትሔ በመስጠት የኢንቨስትመንት ፍሰት እንዲጨምር ማድረግ፣ እንዲሁም ግልጽ እና ውጤታማ የባለሀብቶች ቅሬታ የሚስተናገድበት ሥርዓት ማበጀት በሚያስችል መልኩ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ረቂቅ ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቧል፡፡ ም/ቤቱም በረቂቅ ደንቡ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማከል ተቀብሎ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar