ፓርቲው አቤቱታውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በደብዳቤ ማሳወቁን ጠቁሟል።
የፓርቲው ሊቀ-መንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ ፓርቲው መሰረቱን ትግራይ ክልል በማድረግ ለኢትዮጵያ ህዝቦች ነጻነት፣ እኩልነትና ብልጽግና የሚታገል ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ለዚህም አባላቶቹን በመመልመልና በማብቃት በትግራይ ክልል የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
ይሁንና አባሎቻቸው ላይ በተደጋጋሚ ችግር እየደረሰ መሆኑንና የሚደርሰውን እንግልት ለሚመለከተው አካል በተደጋጋሚ በቃልና በጽሁፍ ማሳወቃቸውን አመልክተዋል።
በተለያዩ የትግራይ ክልሎች የሚገኙ የፓርቲው አባላት ከህግ አግባብ ውጪ ታስረው እየተሰቃዩ ነው ሲሉም ተናግረዋል ሊቀመንበሩ።
ለአብነትም በሽሬ ከተማ በፌስቡክ ጽፋችኋል ተብለው 128 ወጣቶች የታሰሩ ሲሆን በመቀሌ፣ በእንዳስላሴ፣ በዓዲግራት፣ አድዋ፣ እንትጮ፣ ኮረም፣ ወጀራት፣ ዓዲጉደም፣ ቆራሪት፣ ማይሃንሰ፣ ሁመራ፣ሽራሮ፣ ባድመና ሌሎችም ከተሞች የፓርቲው ደጋፊዎች ናችሁ በሚል ታስረው እየተሰቃዩ ነው ብለዋል።
ፓርቲው ለኢዜአ በላከው መግለጫ “ህወሃት በትግራይ ህዝብ፣ በትዴፓና በሌሎችም ሰላማዊ ፓርቲዎች ላይ የአገሪቱን ህገ-መንግስትና ሌሎችንም ህጎች በመጣስ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ጭቆና እያደረሰ በመሆኑ የፌዴራል መንግስት መፍትሄ ይስጠኝ” ሲል ጠይቋል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating