0
0
Read Time:34 Second
በጋምቤላ ክልል በኮሮና የተጠረጠሩ ሰዎች ከለይቶ ማቆያ እየጠፉ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ ማስታወቁን ዶቼ ቨለ አስነብቧል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ኡጁሉ እንደተናገሩት በለይቶ ማቆያነት ከሚያገለግለው ከጋምቤላ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ጊዜያት ያመለጡ ሰዎች ቁጥር 18 ደርሷል።
ሰዎቹን ፈልጎ ማግኘቱ አስቸጋሪ እንደሆነ የጠቀሱት ሃላፊው ከመካከላቸው እስካሁን የተገኘ አለመኖሩን አስረድተዋል።
የክልሉ ነዋሪዎች በሽታው የለም መመርመሪያውም በትክክል አይመረምርም የሚሉና ሌሎች የተሳሳቱ አመለካከቶችን እንደሚያንጸባርቁ የገለጹት ዶ/ር ኡጁሉ ህዝቡ ስለ በሽታው ያለው ግንዛቤ አናሳ መሆን #አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል።
አብዛኛዎቹ የኮሮና ታማሚዎች ምልክት ስለማያሳዩ ብዙዎች በሽታው የለም የሚል እምነት እንዳደረባቸው ዶክተር ኡጁሉ ተናግረዋል።
በጋምቤላ ክልል እስካሁን በበሽታው የተያዙት ሰዎች ቁጥር 180 የደረሰ ሲሆን 54 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንደሚገኙ የዶቼ ቨለ መረጃ ያሳያል
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating