0
0
Read Time:39 Second
**********************************
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ሙሌት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የውሃ ሙሌቱ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ክረምቱ ገና ሳይገባደድ የመጀመሪያው ዙር ሙሌቱ በጥቂት ቀናት ሞልቶ መጠናቀቁና መፍሰስ መጀመሩ ለአገሪቱ ትልቅ የድል ምዕራፍ መክፈቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ ላደረገው የኢትዮጵያ ህዝብና በድርድር ሂደት ሙያዊና የዜግነት ግዴታቸውን ለተወጡት ተደራዳሪዎች እንዲሁም ግድቡን አሁን ላለበት ደረጃ እንዲበቃ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የአገሪቱ የቀድሞ መሪዎችም ጭምር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአሁኑ ሙሊት በሁለት ተርባይን ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል ምዕራፍ መሆኑን የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ የግድቡ ግንባታ ዳር እንዲደርስ በዲፕሎማሲውም ሆነ በግንባታው ሂደት ገና ብዙ ሂደት ይቀረዋል ብለዋል።
በመሆኑም ህዝብና መንግስት በተባበረ ጥረት ለአገራዊ ለውጥና ተጠቃሚነት በጋራ መስራታቸውን እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
የግድቡን ህልውና በዘላቂነት ለማረጋገጥም በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating