www.maledatimes.com አሜሪካ ሶማሊያ በሚገኙ የአይ.ኤስ.አይኤስ ታጣቂዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰነዘረች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

አሜሪካ ሶማሊያ በሚገኙ የአይ.ኤስ.አይኤስ ታጣቂዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰነዘረች

By   /   July 23, 2020  /   Comments Off on አሜሪካ ሶማሊያ በሚገኙ የአይ.ኤስ.አይኤስ ታጣቂዎች ላይ የአየር ጥቃት ሰነዘረች

    Print       Email
0 0
Read Time:37 Second

************************************

የአሜሪካ ጦር ኃይል ማክሰኞ ዕለት ሶማሊያ ውስጥ በሚገኙ እና አሜሪካ በምትደግፋቸው ኃይሎች ላይ ጥቃት የፈጸሙ የአይኤስአይኤስ ታጣቂዎችን ዒላማ ያደረገ የአየር ጥቃት መፈጸሙን ሲኤንኤን አስነብቧል።

“የአሜሪካ-አፍሪካ ኮማንድ የሶማሊያ አይኤስአይኤስ አሸባሪዎች ላይ የአየር ጥቃቱን የፈጸመው ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ቲምሪሽ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የኮማንዱ አጋር ኃይሎች ላይ ቡድኑ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ መሆኑን” የአፍሪካ ኮማንዱ ረቡዕ ዕለት ባወጣው መግለጫ አትቷል።

አያይዞም “የአየር ጥቃቱ ሲሰነዘር የአሜሪካ ኃይሎች ሶማሊያንና አጋር ኃይሎችን ለማማከር እና ለማገዝ በአካባቢው ነበሩ” ብሏል።

ቲምሪሽ ከቦሳሶ ከተማ ደቡብ ምሥራቅ 140 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ስፍራ መሆኗም ተገልጿል።

“በአየር ጥቃቱ የሶማሊያው አይኤስአይኤስ ሰባት አሸባሪዎች ተገድለዋል” ሲል የአፍሪካ ኮማንድ ገልጿል።

የሶማሊያው አይኤስአይኤስ ከዋነኛው አሸባሪ ቡድን ጋር ትስስር ያለው አካባቢያዊ ኃይል ሲሆን፣ ቀደም ሲል በዋናነት በሶማሊያ ሰሜን ምሥራቅ በምትገኘው ፑንትላንድ ግዛት ይንቀሳቀስ ነበር ተብሏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar