www.maledatimes.com የግድቡ ውኃ ሙሌት መካሔድ የህወሓትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ያከሸፈ መሆኑ ተገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የግድቡ ውኃ ሙሌት መካሔድ የህወሓትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ያከሸፈ መሆኑ ተገለጸ

By   /   July 23, 2020  /   Comments Off on የግድቡ ውኃ ሙሌት መካሔድ የህወሓትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ያከሸፈ መሆኑ ተገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:51 Second

*****************************************
የህዳሴው ግድብ ውኃ ሙሌት ህወሓት በፕሮጀክቱ ላይ የሚነዛውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ያከሸፈ ነው ሲሉ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለፁ።

ርእሰ መስተዳድሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ግድቡ የመጀመሪያ ዙር ውኃ ሙሌት ላይ በመድረሱ መላው ኢትዮጵያዊያንን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

ግድቡ ባጋጠሙት ችግሮች ግንባታው መዘግየቱን ያስታወሱት አቶ አሻድሊ የውኃ ሙሌት እንዲጀመር የለውጥ ኃይሉ የኢትዮጵያ ህዝብን በማስተባበር በአጭር ጊዜ ወስጥ የወሰደው የማስተካከያ እርምጃ ውጤት እንደሆነ ተናግረዋል።

በተለይም በህወሓት በኩል በግድቡ ላይ ሲነዙ የነበሩ የሀሰት ፕሮፖጋንዳዎችን ያከሸፈ ነው ብለዋል።

ሀገራዊ ለውጥ ባይመጣ ኖሮ ፕሮጀክቱ በዚህ ወቅት ለውኃ ሙሌት እንደማይደርስ በእርግጠኝነት መናገር እንደሚቻልም ርእሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

የግድቡ ውኃ ሙሌት መከናወኑ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ ታላቅ መነቃቃትና ተስፋ መፍጠሩንም ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በሀሰት ፕሮፖጋንዳው የተታለሉ ግለሰቦችን ግድቡ ተሽጧል የሚለውን ወሬ የከሸፈ መሆኑን በመረዳት ከመንግስት ጎን እንዲቆሙ ርእሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

የጊዜ ጉዳይ እንጂ በለውጡ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ሁሉ እየተጠናቀቁ የሀገራችን ብልፅግና የሚፋጠንበትና የለውጥ አደናቃፊዎች ደግሞ ወደ ኋላ የሚቀሩበት ጊዜ ቅርብ ነው ብለዋል።

ግድቡ የኢትዮጵያውያንን ህዳሴ ለማፋጠን እንጂ ሌሎችን ለመጉዳት እንዳልሆነ የተፋሰሱ ሀገራትም ሊረዱት ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

መላው ኢትዮጵያውያን ግድቡን እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩም ርእሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar