0
0
Read Time:42 Second
“አቶ ለማ መገርሳ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልነታቸዉ ይቀጥላሉ” |የጨፌ ኦሮሚያ ጽ/ቤት ሪፖርተር ጋዜጣ አቶ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን እና ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልነታቸዉ ታግደዋል በማለት ይዞት የወጣዉ ዜና ሀሰት ነዉ ሲል የኦሮሚያ ክልል ኮሚውኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል፡፡ አቶ ለማ መገርሳ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልነታቸዉ ይቀጥላሉ ያለው ቢሮው ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን እና ዶ/ር ሚልኬሳ ሚደጋ አስቀድሞኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት አይደሉም ሲልም ገልጿል፡፡ቢሮው በተለያዩ ምክንያት በተጓደሉ የፌዴሬሽን ምክርቤት አባላት ቦታ መተካካት መኖሩንም አንስቷል፡፡ በዚህም አቶ ፈቃዱ ተሰማ፣ አቶ ሳዳት ነሻ እና አቶ አብዱልሀኪም ሙሉ የፌዴሬሽን ምክርቤት አባላት በነበሩት አምባሳደር እሼቱ ደሴ (በአምባሳደርነት አየርላንድ ተመድበዉ በማገልገል ላይ ያሉ)፣ አቶ በከር ሻሌ (ኮሪያ ሀገር ትምህርት ላይ ያሉ) አቶ ሙክታር ከድር (ኮሪያ ሀገር ትምህርት ላይ ያሉ) የተተኩም ናቸው ብሏል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating