0
0
Read Time:39 Second
የቀድሞው ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ የጥበቃ ኃላፊ የኮሮና ቫይረስ የተገኘበት ሲሆን እሳቸዉ እና ቤተሰቦቻቸው በተደረገላቸዉ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መባላቸዉን በቲዉተር ገፃቸዉ ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ራሳቸውን አግልለዋል! ትናንት ምሽት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በተተረከ ዘጋቢ ፊልም ምርቃት መርሀ ግብር ላይ በክብር እንግድነት ተጋብዘው መገኘት ያልቻሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በኮሮና ቫይረስ በመጠርጠራቸው ምክንያት ራሳቸውን አግልለው ነው ተብሏል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት ተጋብዘው ያልተገኙት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው ራሳቸውን አግለው ነው በማለት ለተጋባዥ እንግዶች ያሳወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ከአሀዱ ኤፍ ኤም ሬድዮ 94.3 የተጠየቁት የቀድሞዋ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ሲሉ መልሰዋል። https://youtu.be/ZnSUYCZPsfE
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating