www.maledatimes.com በመቀለ ‘ሕገወጥ ሰልፍ ሊያካሂዱ ሲሉ ተይዘዋል’ የተባሉ ዘጠኝ ወጣቶች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በመቀለ ‘ሕገወጥ ሰልፍ ሊያካሂዱ ሲሉ ተይዘዋል’ የተባሉ ዘጠኝ ወጣቶች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው!

By   /   August 14, 2020  /   Comments Off on በመቀለ ‘ሕገወጥ ሰልፍ ሊያካሂዱ ሲሉ ተይዘዋል’ የተባሉ ዘጠኝ ወጣቶች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው!

    Print       Email
0 0
Read Time:52 Second

በመቀለ ‘ሕገወጥ ሰልፍ ሊያካሂዱ ሲሉ ተይዘዋል’ የተባሉ ዘጠኝ ወጣቶች ላይ የትግራይ ፓሊስ ምርመራውን በመጨረሱ ፋይላቸውን ክስ እንዲመሰረት ወደ ዐቃቤ ሕግ ማስተላለፉን ገልጿል። ከዚህ ቀደምም ሦስት ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረባቸውንና ከሰባት ቀን በኋላ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ነው ቢቢሲ የዘገበው።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ወጣቶቹ ከ46 ቀናት በፊት፣ ሐምሌ ወር መጀመሪያ ላይ በመቀለ የሮማነት አደባባይ ላይ መንግሥትን በኃይል ለመጣል የሚያነሳሳ መፈክር ይዘው መገኘታቸውን እንዲሁም ያልተፈቀደ ሠልፍ ለማካሄድ ሲወጡ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ገልጾ ነበር። ዘጠኙ ወጣቶች በሐምሌ ወር መጀመሪያ አካባቢ ላይ የክልሉን መንግሥት በመቃወም ሕገወጥ የተቃወሞ ሰልፍ ሊያካሂዱ ነበር በሚል በፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኀላ በወቅቱ በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ፖሊስ በተደጋጋሚ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ በመጠየቅ ከ46 ቀናት በላይ በእስር ላይ ቆይተዋል።

እስከ አሁን ድረስ የፍትህ ውሳኔ ያልተሰጣቸው ሲሆን በመቀሌ የሚገኘው አስተዳደር ከዚህ ቀደም ያደርገው የነበረውን አይነት ስርአት በመቀሌ ገንብቶ ህዝብን በግፍ እያሰረ እና እየጨቆነ ነው ሲሉ የፈንቅል አባላቶች ለማለዳ ተናግረዋል፡፤ እንደ ፈንቅል አባላቶች አባባል ከሆነ የትግራይ ክልል መንግስት በትግራይ ህዝብ ላይ የሚያደርገው ጭቆና የከፋ ከመሆኑም በላይ አሰቃቂ ነው ፣ ህብረተሰቡ የግፍ ቀንበር ተሸክሞ ነው የሚዞረው፣ በዚህም ጉዳይ ላይ የፌደራል መንግስትም ለህዝቡ ምንም ትኩረት አልሰጠውም ሲሉ ተናግረዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar