0
0
Read Time:25 Second
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ እንደገለጹት በቀጣዩ ዓመት ፈቃዱን ከሚያገኙት መካከል በጨረታ ያሸነፉ ሶስት የኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ይገኙበታል። እንዲሁም ማስረጃዎችን አሟልተው ያቀረቡ የሳተላይት ጣቢያ ፈቃድ ፈላጊዎች ወዲያውኑ ይስተናገዳሉ ብለዋል።
ፈቃዱ የሚሰጠው ፍላጎትን በማመጣጠንና ያለውን ምጥን የሆነ የአየር ሞገድ ታሳቢ በማድረግ መሆኑንም ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል። የሕትመት መገናኛ ብዙኃንን ለማስፋፋት ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ፈቃድ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።
በመገናኛ ብዙኃን የሚስተዋለውን ያልተገባ አካሔድን በማስከን ዘርፉን ወደፊት በማራመድ ረገድ በኃላፊነት ስሜት መስራት እንደሚያስፈልግም ጠቅሰዋል። ባለስልጣኑ በዚህ ዓመት ለሶስት የኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ፈቃድ መስጠቱ ታውቋል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating