www.maledatimes.com የፍርድ፡ቤት፡ችሎት፡በእነ፡ጃዋር፡መሃመድ፡ላይ፡ያሳለፈው፡ውሳኔ፡አግባብ፡አይደለም። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የፍርድ፡ቤት፡ችሎት፡በእነ፡ጃዋር፡መሃመድ፡ላይ፡ያሳለፈው፡ውሳኔ፡አግባብ፡አይደለም።

By   /   August 28, 2020  /   Comments Off on የፍርድ፡ቤት፡ችሎት፡በእነ፡ጃዋር፡መሃመድ፡ላይ፡ያሳለፈው፡ውሳኔ፡አግባብ፡አይደለም።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 15 Second

ሙሉ ነጻነት ሊሰጣቸው አይገባም፣ አንዱን ልጅ አንዱን እንጀራ ልጅ አድርጎ ፍርድቤቱ ያያል ።

 
 
 
 
 
 
 
 

 

 
ችሎት!
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ14ቱም ተጠርጣሪዎች ላይ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ለመስማት ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አቶ ጃዋር መሃመድን ጨምሮ ከአራተኛ እስከ 14ኛ የተዘረዘሩ ተጠርጣሪዎች የኮቪድ-19 ምርመራ ተደርጎላቸው ነፃ መሆናቸውን የሚገልፅ ውጤት ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል።
ከዚህ በፊት አቶ ጃዋር መሀመድና አቶ በቀለ ገርባ ከጓደኞቻቸው ጋር መገናኘት አልቻልንም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ፍርድ ቤቱ በጓደኛ የመጠየቅ መብት ቢኖራቸውም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚከለክል በመሆኑ አልተቀበለም።
አንደኛ ተጠርጣሪ የሆኑት አቶ ጃዋር መሃመድ ከልጄ እና ከባለቤቴ ጋር በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንድገናኝ ይፈቀድልኝ ሲሉ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ በሳምንት ሁለት ጊዜ በቪዲዮ ኮንፍረንስ እንዲገናኙ አዟል።
12ኛ ተጠርጣሪ የሆኑት አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ጆሮዬን ታምሚያለሁ የተሻለ ሆስፒታል ልታከም ብለው አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤት በመረጡት ሆስፒታል እንዲታከሙ እንዲመቻችላቸው አዟል።
ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በአጠቃላይ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ ቀሪ ምስክሮችን ለማድመጥ ለፊታችን ማክሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
Tiblets

 

 

ችሎት!

ፍርድ ቤት አርቲስትሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል በተጠረጠሩት ከበደ ገመቹ እና አብዲ ዓለማየሁ ላይ አቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰርት የ15 ቀን ጊዜ ሰጠ።
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፖሊስ ምርመራዬን አጠናቅቂያለሁ ብሎ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ አስረክቧል።
በችሌቱ አንደኛው ተጠርጣሪ አብዲ ዓለማየሁ ሃጫሉ ሁንዴሳ በተገደለበት ወቅት በቦታው አልነበርኩም ያለ ሲሆን ሌላኛው ተጠርጣሪ ጥላሁን ያሚ በበኩሉ አርቲስቱ ሲገደል ከበደ ገመቹና አብዲ ዓለማየሁ አብረውት እንደነበሩ አስረድቷል።
በዚሁ መሰረትም ፍርድ ቤቱ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የክስ መመስረቻ አስራ አምስት (15) ቀን ጊዜ ተሰጥቷል
 
 
 
 
 
 
Happy
Happy
100 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar