0
0
Read Time:30 Second
የኦሞ ወንዝ ሞልቶ ዉኃ ከከባቸዉ መንደሮች ለማምለጥ የሞከሩ አራት የደቡብ ክልል ፤ የዳሰነች ወረዳ ነዋሪዎች ሞቱ።
የአካባቢዉ ባለስልጣናት ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ እንዳሳወቁት አራቱ ሰዎች በዉኃ የተበሉት ዉኃ ከከበባት ቶል-ታሌ ቀበሌ ወደ ደረቅ መሬት በጀልባ ለመሻገር ሲሞክሩ ጀልባቸዉ ተገልብጣ ነዉ።
ከሟቾቹ ሁለቱ እናት እና ልጅ ሁለቱ ደግሞ አዛዉንቶች ነበሩ።
በውኃ ተከበው የነበሩ ሌሎች 200 ነዋሪዎች ግን ከክልሉ በተላኩ ጀልባዎች ርዳታ ሙሉ በሙሉ ወደ ደረቅ አካባቢ መሻገራቸዉን ተሰምቷል።
የኦሞ ወንዝ ሙላት ከዳሳች ወረዳ አርባ (40) ቀበሌዎች መካከል 28ቱን አጥለቅልቋል። ከ15 ሺሕ በላይ ሰዎችን ከቤት ንብረታቸዉ አፈናቅሏል።
የዉኃ ሙላቱ ከ30 ዓመት ወዲሕ ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ ያሁኑ የመጀመሪያዉ መሆኑን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating