0
0
Read Time:31 Second
በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በምግብ፣ በአልባሳት እና በመጠለያ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለአብመድ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የተጠየቀው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ታረቀኝ ተሲሳ ከኅዳር 5 ጀምሮ ከተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በድባጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ 1 ሺህ 200 ተፈናቃዮች 180 ኩንታል እህል እና 20 ኩንታል የህፃናት አልሚ ምግብ እንዲሁም ሦስት ቦንዳ ልብስ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ በዘላቂነት ለማቋቋም ቀጣናው በኮማንድ ፖስት እየተመራ እንደሆነ ኮሚሽነር ታረቀኝ አንስተዋል፡፡ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ይደረጋል፤ መልሶ የማቋቋም ሥራም ይስራል ብለዋል። በአካባቢው ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating