0
0
Read Time:29 Second
#ጥንቃቄ
ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት ጋር ተያይዞ በተለያዩ የሀገራችን ድረ-ገጾች ላይ የመረጃ መበርበር ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል የተባለ ቡድን አሁን ላይ 37 ሺህ በሚደርሱ ኮምፒውተሮች ላይ የሳይበር ጥቃት ለመፈፀም ሙከራ እያደረገ መሆኑ ተገለፀ።
ይህን ያሳወቀው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ነው።
ተቋሙ ባወጣው መረጃ “ሳይበር ሆርስ ግሩፕ” የተሰኘው የመረጃ ሰርሳሪ ቡድን አዲስ የኮምፒውተር ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች ላይ ለመልቀቅ ዝግጅት ማድረጉ እንደተደረሰበት ገልጿል።
ቫይረሱ “ብላክ ፒራሚድ ዋር” የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን 37 ሺህ በሚደርሱ የሀገራችን ኮምፒውተሮች ላይ ማነጣጠሩ ተገልጿል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ሁሉም የሳይበር ምህዳሩ ተጠቃሚዎች ተገቢውን የሳይበር ደህንነት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating