www.maledatimes.com በአዲስ አበባ ጎዳና ተዳዳሪ በመምስል ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ 1 ሺ የሚጠጉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአዲስ አበባ ጎዳና ተዳዳሪ በመምስል ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ 1 ሺ የሚጠጉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

By   /   June 1, 2021  /   Comments Off on በአዲስ አበባ ጎዳና ተዳዳሪ በመምስል ልዩ ልዩ ወንጀሎችን በመፈፀም ለፀጥታ ስጋት የሆኑ 1 ሺ የሚጠጉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

    Print       Email
0 0
Read Time:50 Second

#AddisAbaba

ፖሊስ የምርመራ ስራ እየሰራ ይገኛል።

ተጠርጣሪዎቹ ከህዝብ በደረሰ መረጃ መነሻ በማድረግ በ7 ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 20 ቦታዎች ላይ ግንቦት 22 ቀን 2013 በተከናወነ የኦፕሬሽ ስራ የተያዙ ናቸው።

አጠቃላይ ቋሚ አድራሻ የሌላቸውና በዋና ዋና አደባባዮች እና በምሽት በሰዋራ ቦታዎች የተለያዩ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ የነበሩ 999 ግለሰቦች ናቸው የተያዙት።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል ፦

– አብዛኞቹ ማስቲሽና ቤንዚን በመጠቀም እራሳቸውን በማደንዘዝ የትራፊክ እንቅስቃሴዎችን ሲያውኩ እነደነበሩ

– የትራፊክ መብራት ካስቆመው ተሽከርካሪ ላይ ስፖኪዮ ገንጥለው እንደሚወስዱ፣

– ከአሽከርካሪ ወይም ከተሳፋሪ ላይ ሞባይል ስልክ፣ የአንገት ሃብል፣ ቦርሳ እና ልዩ ልዩ ንብረቶችን ቀምተው እንደሚሰወሩ

– በተለይ ሴት አሽከርካሪዎች አደጋ ሳያደረሱባቸው አደጋ እንዳደረሱባቸው በማስመሰልና በማዋከብ ገንዘብ እንደሚቀበሉ፣

– የትራፊክ አደጋ ሲያጋጥም ልዩ ልዩ ስልቶችን በመጠቀም ንብረቶችን እንደሚሰርቁ በጥቅሉ ትኩረታቸውን በዋና ዋና አደባባይ የትራፊክ መብራት በያዘው ተሽከርካሪ ላይ አድርገው ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር ተረጋጧል።

በሌላ በኩል ግለሰቦቹ በምሽት የቅሚያ ወንጀል ሲፈፅሙ እንደነበር የተረጋገጠ ሲሆን በተለይ ደግሞ የውጪ ሀገር ዜጎችንና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡን በማዋከብና በማስጨነቅ በከተማዋ መልካም ገፅታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሲፈጥሩ ነበር።

የተሰወኑት ግለሰቦች ደግሞ የጎዳና ተዳዳሪ በመምስል የሽብር ተግባር ለማስፈፀም ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸውን የአ/አ ፖሊስ በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 4 years ago on June 1, 2021
  • By:
  • Last Modified: June 1, 2021 @ 2:07 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar