www.maledatimes.com የጠፋች ልጃቸውን በሕይወት ለማግኘት ተስፋ ያደረጉት ቤተሰቦች አስከሬኗን ተረክበዋል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

የጠፋች ልጃቸውን በሕይወት ለማግኘት ተስፋ ያደረጉት ቤተሰቦች አስከሬኗን ተረክበዋል

By   /   June 1, 2021  /   Comments Off on የጠፋች ልጃቸውን በሕይወት ለማግኘት ተስፋ ያደረጉት ቤተሰቦች አስከሬኗን ተረክበዋል

    Print       Email
0 0
Read Time:55 Second

!

የ16 ዓመቷ ተማሪ ፌቨን ዳዊት ከጠፋች ከ4 ቀናት በሗላ አስክሬኗ በሀዋሳ ሀይቅ ተገኘ።

ፌቨንና ጓደኛዋ ትዕግስት ዘወትር እንደሚያደርጉት ሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ እየተዝናኑ ነበር በድንገት 2 ወጣቶች ካልተቀላቀልናችሁ ብለው አብረዋቸው የሆኑት።

ጥቂት ደቂቃዎችን አብረዋቸው ከቆዩ በሗላ በጀልባ ሀይቁ ላይ እንዝናና የሚል ጥያቄን ወጣቶቹ ያነሳሉ። 2ቱ ታዳጊ ሴቶች አለመፈለጋቸውን ቢገልፁም የወጣቶቹ ጉትጎታ የሚቻል ስላልነበር እሺ ለማለት ተገደዱ።

ጏደኛዋ ትዕግስት እንደምትለው የታዳጊ ሴቶቹ ቀጣይ ፈተና የነበረው የጀልባ ጉዞው ለየብቻ ነው የሚል ትዛዝ አዘል መመሪያ ከወንዶቹ ሲመጣ ነው።

ብዙ አታስቡ ተከታትለን ስለምንሄድ የሚል የማሳመኛ ቃል ሲደጋገም እሺታን መርጠው ጉዞ ጀመሩ።

አላማቸው 2ቱን ታዳጊ ሴቶች መነጠል እንጂ መዝናናት ስላልነበር አንደኛው ወጣት ፌቨንን ይዞ ጉዞ ይጀምራል..ጥቂት እንደተጓዙ ፌቨን የነ ትዕግስትን ጀልባ መመልከት ስላልቻለች ከወዴት ናችሁ የሚል ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ለጓደኛዋ ታደርጋለች።

ከቆይታ በሗላ የት ናችሁ የሚል ጥያቄ ሳይሆን ለጓደኛዋ የድረሽልኝ መማፀኛ መልዕክት መላክ ጀመረች።

አሳዛኙ እውነታ ግን ፌቨን ከሀይቁ ሰምጣለች። ወጣቶቹ ከአካባቢው ተሰውረዋል።

ከ4 አስጨናቂ ቀናት በኋላ ቤተሰብ የ16 አመት ልጃቸውን አስክሬን ተረክበዋል።

የፌቨን አስክሬን ሲገኝ እጇ መጠምዘዙን ዓይኗ በቦክስ የመመታት ምልክት እንደነበረው በቦታው ቤተሰቦቿ ይናገራሉ።

2ቱን ወጣቶች ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያደረገ ይገኛል።

ህይወትን አይታ ያልጠገበችው የ16 ዓመቷ ፌቨን ቤተሰቦች ፈጣሪ እውነቱን ያሳየን የፍትህ ያለህ ይላሉ!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar