www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስተር የሆኑት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ የኤርትራን ሰራዊትን ከኢትዮጵያ የማስወጣት ሂደት መጀመሩን ገለፁ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስተር የሆኑት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ የኤርትራን ሰራዊትን ከኢትዮጵያ የማስወጣት ሂደት መጀመሩን ገለፁ።

By   /   June 4, 2021  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስተር የሆኑት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ የኤርትራን ሰራዊትን ከኢትዮጵያ የማስወጣት ሂደት መጀመሩን ገለፁ።

    Print       Email
0 0
Read Time:42 Second

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስተር የሆኑት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ የኤርትራን ሰራዊትን ከኢትዮጵያ የማስወጣት ሂደት መጀመሩን ገለፁ።

አገር መከላከያ ሚኒስትሩ ይህን የገለፁት በዛሬ ዕለት የኢፊድሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ ጉዳይ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ ነው።

ዶክተር ቀነዓ ፥ የኤርትራን ጦር ከኢትዮጵያ የማስወጣት ሂደት መጀመሩን ከመግለፅ ባለፈ የሕወሓት ኃይል ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጋር መዋጋት በሚያስችለው ቁመና ላይ አይደለም ሲሉም ተደምጠዋል።

ሕወሓት በቀበሌዎች ላይ የደፈጣ ጥቃት ለማድረስ እየሞከረ መሆኑን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ መድረክ ላይ ተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሹመቴ ይግዛው በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ የረድዔት ተቋማት ሰራተኞች የሚጠቀሙባቸው የኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ለወታደራዊ አገልግሎት ሊውሉ እንደማይችሉ ገልፀዋል።

ዶ/ር ሹመቴ ይግዛው ፥ ያልተፈቀዱ የኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ደብቀው ለማሳለፍ ሲሞክሩ የተያዙ የእርዳታ ድርጅቶች መኖራቸውንና ኢትየጵያዊ ሰራተኞቻቸውን ከስራ እያሰናበቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ በምንም መንገድ ‘አይፈቀድም’ ሲሉ ዳይሬክተሩ አስጠንቅቀዋል።

ዳይሬክተሩ ፥ “የሰብዓዊ ድርጅቶች ድርጊት ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት ሊሆኑ አይገባም፤ ይህ ሆኖ ከተገኘም “እርምጃ ይወሰዳል።” ሲሉ አሳስበዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar