0
0
Read Time:40 Second
በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 – ሰኔ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮ ይህን የገለፀው ዛሬ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክቶ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።
መግለጫዉን የሰጡት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ሙላው አበበ ሲሆኑ የ2013 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሰኔ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተናግረዋል።
በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎቻቸው ፈተናዉን የሚወስዱበትን ቀን እንዲያሳውቁ ምክትል ኀላፊው አሳስበዋል።
በትምህርት ወደኋላ የቀሩ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት እንዲሰጣቸው፤ ተማሪዎች የፈተናውን ቀን አውቀው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው አቶ ሙላው የገለጹት።
ፈተናው በሚሰጥበት ቀንም ኾነ የፈተናው የጥያቄ ወረቀት የማጓጓዝ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲኾን በየዘርፉ የሚገኙ የጸጥታ አካላት ኀላፊነታቸዉን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
በአማራ ክልል ከ500 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ፈተናን የሚሰጡ ሲኾን 420 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ መታወቁን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating