www.maledatimes.com “… በሚቀጥለው ጊዜ ኋይት ሀውስ ‘ስገባ’ በእሱ ጥያቄ ከማርክ ዙከንበርግ እና ባለቤቱ ጋር የእራት ግብዣ ብሎ ነገር አይኖርም” – ዶናልድ ትራምፕ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

“… በሚቀጥለው ጊዜ ኋይት ሀውስ ‘ስገባ’ በእሱ ጥያቄ ከማርክ ዙከንበርግ እና ባለቤቱ ጋር የእራት ግብዣ ብሎ ነገር አይኖርም” – ዶናልድ ትራምፕ

By   /   June 5, 2021  /   Comments Off on “… በሚቀጥለው ጊዜ ኋይት ሀውስ ‘ስገባ’ በእሱ ጥያቄ ከማርክ ዙከንበርግ እና ባለቤቱ ጋር የእራት ግብዣ ብሎ ነገር አይኖርም” – ዶናልድ ትራምፕ

    Print       Email
0 0
Read Time:39 Second

የቀደሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለሁለት ዓመት መታገዳቸውን ተከትሎ መግለጫ አውጥተዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ባወጡት መግለጫ “የፌስቡክ ውሳኔ 75 ሚሊዮን ሰዎችን ጨምሮ ለመረጡን ብዙ ሰዎች ስድብ ነው …” “በዚህ ሳንሱር እና ማፈን እንዲቀጥሉ ሊፈቀድላቸው አይገባም። በመጨረሻም እኛ እናሸንፋለን። ሀገራችን ከእንግዲህ ይህን በደል መሸከም አትችልም!” ብለዋል።

ትራምፕ በሰጡት መግለጫ በፌስቡክ መስራች ላይ ትችት ሰንዝረዋል።

በቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ብርቱ ተፎካካሪ ለመሆን ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የገለፁት ትራምፕ ዳግም ወደ ኋይት ሀውስ ሲመጡ ከማርክ ዙከርበርግ እና ባለቤታቸው ጋር እራት እንደማይኖራቸው ተናግረዋል።

ትራምፕ ፥ “በሚቀጥለው ጊዜ በኋይት [ስገባ] በእሱ ጥያቄ ከማርክ ዙከንበርግ እና ባለቤቱ ጋር የእራት ግብዣ ብሎ ነገር አይኖርም። ሁሉም ነገር ሥራ ይሆናል!” ብለዋል።

የፌስቡክ ውሳኔ ትራምፕ ከ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት ወደ መድረኩ እንዲመለሱ ያስችላቸዋል።

ከ ፌስቡክ በተጨማሪ ትራምፕ በጥር ወር ካፒቶል ሂል ረብሻ ምክንያት ከትዊተር፣ ዩቲዩብ፣ ስናፕቻት፣ ትዊች እና ከሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ታግደዋል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar