የአፍሪካ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት በደረሰው ጥያቄ መሠረት የአጭር እና የረዥም ጊዜ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድኖችን መላኩን የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ማስታወቃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።
ሰኔ 14 የሚካሄደውን አጠቃላይ ብሄራዊ ምርጫ የሚታዘቡት ከተለያዩ የህብረቱ አባል ሃገሮች የተውጣጡ 8 አባላት የሚገኙበት የረዥም ጊዜ ክትትል ቡድን ሐሙስ እና ረቡዕ አዲስ አበባ መግባቱን የአፍሪካ ህብረት ባወጣው የፕሬስ መግለጫ አመልክቷል።
ቡድኑ በኢትዮጵያ ቆይታው ቁልፍ የሚባሉ የምርጫ ሂደቱ ክፍሎች ላይ ቅኝት እንደሚያደርግና ትንተና እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።
በተለይ የፖለቲካውን አየር፣ የምርጫውን የህግ ማዕቀፍ፣ የምርጫ ዝግጅቱን ውጤታማነትና ግልፅነት እንዲሁም የአስተዳደርና የመገናኛ ብዙኃን ነፃነትንና በመላ ሂደቱ ውስጥ ለተሣትፎ መብቶች መከበር የሚሰጠውን ትኩረት ጨምሮ የዘመቻውን አካሄድ ሁኔታ እንደሚያካትት አስታውቋል።
የረዥም ጊዜ ታዛቢ ቡድኖች በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚሰማሩ የአፍሪካ ኅብረት ጠቁሞ ምርጫው ሊካሄድ ወደ አንድ ሳምንት ሲቀር ብርካታ የአጭር ጊዜ ታዛቢ ቡድኖች አዲስ አበባ እንደሚገቡ ገልጿል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠማራው የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ተልዕኮ በህብረቱ ድንጋጌዎች መሠረት በምርጫው ሂደት ላይ መረጃ የመሰብሰብና የመተንተን መብትና ችሎታ እንዳለው የፕሬስ መግለጫ በተለያዩ ጊዜዎች የወጡና የተፈረሙ ውሎችና መግለጫዎችን አጣቅሶ አስታውቋል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating