www.maledatimes.com በኢትዮጵያ “በቀን በአማካኝ 30 ሰዎች በኤድስ ህይወታቸው ያጣሉ” ተባለ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

በኢትዮጵያ “በቀን በአማካኝ 30 ሰዎች በኤድስ ህይወታቸው ያጣሉ” ተባለ።

By   /   June 6, 2021  /   Comments Off on በኢትዮጵያ “በቀን በአማካኝ 30 ሰዎች በኤድስ ህይወታቸው ያጣሉ” ተባለ።

    Print       Email
0 0
Read Time:56 Second

በኢትዮጵያ “በቀን በአማካኝ 30 ሰዎች በኤድስ ህይወታቸው ያጣሉ” ተባለ።

ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ በዓለማችን ወረርሽኝ በሽታ ነው ተብሎ ከታወቀ በዛሬው ዕለት 40ኛ ዓመቱ ማስቆጠሩን የተለያዩ መረጃዎች ያሳያሉ። በሀገራችን ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 1981 ተከስቶ እስካሁን በርካታ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ስነ ልቦናዊ ቀውስ ማስከተሉንም እንዲሁ፡፡

በፈረንጆቹ ከ1990 በነበረው የመጀመርያው ዘመን በሽታው እጅግ የተስፋፋበት፣ ትኩረት ያልተሰጠበት፣ በርካቶች ሰለባ የሆኑበት የከፋ ዘመን ነበር።

የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠርያ ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል በትረ ከአል ዓይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል።

በዚህም፦

– የቫይረሱ የስርጭት ምጣኔ እንደ ሀገር 0.93 በመቶ ሲሆን በከተሞች ያለው የስርጭት ምጣኔ ከ3 በመቶ በላይ እንዲሁም በገጠር 0.4 በመቶ ይሆናል።

– አሁን ላይ ቫይረሱ በደማቸው አለ ተብሎ ከሚታሰቡት 622 ሺ በላይ ዜጎች መካከል 61 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። ይህም የሴቶችን የበለጠ የቫይረሱ ተጋላጭነትን ያሳያል።

– ከ100 ሴተኛ አዳሪዎች መካከል 18ቱ ወይም 19ኙ ቫይረሱ ያለባቸው ናቸው።

– በዓመት 11 ሺ ወይም በቀን 30 አዳዲስ ሰዎች (67 በመቶ የሚሆኑት ከ15 እስከ 24 የዕድሜ ክልል የሚገኙ) በቫይረሱ ይያዛሉ።

– በየዓመቱ 12ሺ ወይም በየቀኑ 30 ሰዎች ይሞታሉ።

– በኢትዮጵያ የቫይረሱ የስርጭት ታሪክ 1996 ዓ/ም ከፍተኛ የሟቾች ቁጥር የተመዘገበበት ዓመት ነው። 90 ሺ ያህል ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸውም ይነገራል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar