0
0
Read Time:33 Second
በጉራፈርዳ ወረዳ 6 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ።
6 የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኘው ጉራፈርዳ ወረዳ ውስጥ ትላንት በታጣቂዎች ተገድለዋል።
የልዩ ኃይል አባላቱ የተገደሉት በወረዳው ስር ባለው ወጀምታ ቀበሌ ነው።
“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ” ቃላቸውን የሰጡት የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ሻሎም ፥ ጥቃት የተፈጸመባቸው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት፤ በወጀምታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰንበሊጥ በተባለ ቦታ ባለ ካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
8 የልዩ ኃይል አባላት፤ ትላንት ከጠዋት 2 ሰዓት ገደማ፤ አንድ የካምፑን ሰራተኛ አጅበው ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ሲሄዱ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አስረድተዋል።
በጥቃቱ ስድስት የልዩ ኃይል አባላት ሲገደሉ አብሯቸው የነበረው የካምፑ ሰራተኛ ጉዳት ደርሶበት ህክምና ላይ ይገኛል ብለዋል።
ለአጀባ ከተሰማሩት የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ 2ቱ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸውም ሲሉ ገልፀዋል
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating