0
0
Read Time:35 Second
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ህይወታቸው አለፈ።
ታዋቂው ናይጄሪያው የሃይማኖት ሰባኪ ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ትናንትና ህይወታቸው አለፈ።
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ወይም በተለምዶ ቲቢ ጆሹዋ ማረፋቸውንም ይፈዊ በሆነው ፌስቡክ ገፃቸውም ላይ “አምላክ አገልጋዩን ቲቢ ጆሹዋን ወደቤቱ ወስዷል” በሚልም ሰፍሯል።
ስመ ጥር የሆኑት የኢቫንጀሊካን ሃይማኖት ሰባኪ በትናንትናው ዕለት የቤተክርስቲያን ፕሮግራማቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምሽት ላይ ማረፋቸው ተገልጿል።
በተከታዮቻቸው ዘንድ የነብይነትን ማዕረግ ያገኙት ቲቢ ጆሹዋ በአህጉሪቷ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ የኢቫንጀሊካል ሰባኪዎች አንዱ ናቸው ።
በአፍሪካ ውስጥም ያሉ ታዋቂ ፖለቲከኞችንም በተከታይነት ማፍራት ችለዋል።
“ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽንስ” የሚባል የእምነት ተቋምን የመሰረቱ ሲሆን እንዲሁም በቴሌቪዥንም በሚያደርጓቸው ስብከቶችም በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምዕመናንን ማፍራት ችለዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሌጎስ የሚያደርጓቸውን ሳምንታዊ የአገልግሎት ስርዓት ይከተላሉ ነበር።
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ በ57 ዓመታቸው ነው ህይወታቸው አለፈ።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating