0
0
Read Time:41 Second
#Update
የ “አበበች ጎበና ህፃናት ክብካቤ እና ልማት ማህበር” ከሰዓታት በፊት ባሰራጨው መልዕክት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) አሁንም በጳውሎስ ሆስፒታል በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምና እያገኙ መሆኑን አሳውቋል።
ዶክተሮቻችው ለቤተሰብ እንደገለፁት ጤናቸው በጣም መሻሻል አሳይተዋል፡፡
የልብ፣ የኩላሊት፣ የጉበት፣ የደም ግፊትና የመሳሰሉት ምርመራ ተደርጎላቸው ጥሩ የሚባል ሁኔታ ላይ መሆናቸው ዶክተሮች ገልፀዋል ብሏል ማህበሩ ባሰራጨው መልዕክት።
ማህበሩ ፥ “የጳውሎስ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ደከመኝ ሰለጨኝ ሳይሉ 24 ሰዓታት የእዳዬን ጤና ለመመለስ የህምና እርዳታ ላደረጉላቸው ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርለን” ሲል አመስግኗል።
ወዳጆቻቸው፣ ልጆቻችው እና ሎሎችም ከኢትዮጵያ ና ከተለያዩ ሀገራት በእንዳዬ መታመም ተጨንቀው ስልክ በመደወልና መልዕክት በመላክ የጠየቁትን በአጠቃለይ በፀሎትም አብረው ለሆኑ ሁሉም ማህበሩ አመስግኗል።
በመጨረሻም፥ የሺዎች እናት የሆኑት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ፈጣሪ ጨርሶ ይምራቸው ዘንድ ሁላችንም እንፀልይላቸው ሲል የአበበች ጎበና ህፃናት ክብካቤ እና ልማት ማህበር መልዕክት አስተላልፏል።
ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና በኮቪድ-19 ተይዘው ለህክምና ሆስፒታል መግባታቸው ይታወሳል።
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating