www.maledatimes.com “…ታጣቂዎች መሣሪያ በማቀባበል ጭምር ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም በማለት መንገድ በመዝጋታቸው የምርጫ ቅስቀሳው ሳይካሄድ ቀርቷል” – ኢዜማ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

“…ታጣቂዎች መሣሪያ በማቀባበል ጭምር ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም በማለት መንገድ በመዝጋታቸው የምርጫ ቅስቀሳው ሳይካሄድ ቀርቷል” – ኢዜማ

By   /   June 6, 2021  /   Comments Off on “…ታጣቂዎች መሣሪያ በማቀባበል ጭምር ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም በማለት መንገድ በመዝጋታቸው የምርጫ ቅስቀሳው ሳይካሄድ ቀርቷል” – ኢዜማ

    Print       Email
0 0
Read Time:45 Second

“…ታጣቂዎች መሣሪያ በማቀባበል ጭምር ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም በማለት መንገድ በመዝጋታቸው የምርጫ ቅስቀሳው ሳይካሄድ ቀርቷል” – ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ስሬ ምርጫ ወረዳ ሊያደርግ የነበረው የምርጫ ቅስቀሳ ዝግጅት በአካባቢው አስተዳደር ክልከላ እንደተስተጓጎለበት አመለከተ።

ፓርቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ ፥ የፓርቲው ዋና ጸሐፊ አበበ አካሉ የጎዳና ላይ የምርጫ ለማድረግ ወደስሬ ሄደው የነበረ ሲሆን በስሬ ምርጫ ወረዳ ሻሜዳ ቀበሌ ሊቀመንበር እና የቀበሌው ሥራ አስኪያጅ የተመሩ ታጣቂዎች መሣሪያ በማቀባበል ጭምር ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም በማለት መንገድ በመዝጋታቸው የምርጫ ቅስቀሳው ሳይካሄድ ቀርቷል ብሏል።

ፓርቲው በስሬ ወረዳ ምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ያጋጠመውን ችግር ለምርጫ ቦርድ አመለክታለሁ ብሏል።

ኢዜማ ፥ መጋቢት 3 ቀን 2013 ከምርጫው ሂደት ጋር በተያያዘ ከሌሎች ቦታዎች በተለየም ዕጩ ለማስመዝገብም ሆነ በነፃነት እንቅስቃሴ ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ ከተቸገረባቸው ቦታዎች የኦሮሚያ ክልል አንዱ መሆኑን በመጥቀስ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቆ እንደነበር አስታውሷል።

በተጨማሪም በየአካባቢው በሚገኙ የገዢው ፓርቲ (ብልፅግና) አባላት ምርጫው ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዳይሆነ የሚፈፀሙትን እኩይ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ግንቦት 19 ባወጣው መግለጫ መጠየቁን አስታውሷል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar