www.maledatimes.com የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በምርጫ እለት ድንገተኛ አደጋዎች ቢያጋጥሙ እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችን ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በምርጫ እለት ድንገተኛ አደጋዎች ቢያጋጥሙ እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችን ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

By   /   June 7, 2021  /   Comments Off on የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በምርጫ እለት ድንገተኛ አደጋዎች ቢያጋጥሙ እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችን ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

    Print       Email
0 0
Read Time:45 Second

#EthiopiaElection2013

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በምርጫ እለት ድንገተኛ አደጋዎች ቢያጋጥሙ እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችን ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ቢሮው ፥ ከምርጫ አስቀድሞ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ከምርጫ በኋላ ለሚፈጠሩ ችግሮች ዝግጁ በመሆን እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ጤና ቢሮው የጤና ምርምር ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ዳይሬክተርና የኮቪድ-19 ማስተባበሪያ መዕከል ምክትል አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ዳምጠው ፥ በምርጫ ወቅት ኮቪድ-19 እንዳይስፋፋ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች የሚሰጡና ድንገተኛ አደጋዎች ቢያጋጥሙ ወይም ግጭቶች ቢኖሩ እርዳታ የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ በትምህርት ቤቶች ላይና በመገናኛ ብዙኃን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ይሰራል ብለዋል።

አቶ ዳንኤል ፥ በምርጫ ወቅት ድንገተኛ አደጋዎች ቢያጋጥሙም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሰው ኃይልን በማደራጀት፤ የጎደሉ ህክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶችን የሟሟማላት ስራ እንደተጀመረና ቀጣይነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያዎች ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ዳንኤል ከምርጫው በኋላም የኮሮና ቫይረስ ሊስፋፋ ስለሚችል ሌላ ተጨማሪ 5 መቶ የጽኑ ህሙማን አልጋዎች ዝግጁ መደረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ሌሎች የጤና ስጋቶችም ካሉ በአቅራቢያ የሚገኙ 20 የጤና ተቋማትና እንዲሁም ሌሎች የግል የጤና ተቋማትን ዝግጁ በማድረግ ቢሮው መስራቱን ገልጸዋል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar