www.maledatimes.com ቬሮኒካ በአድማጭ ትካዜ ተመታች:: - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቬሮኒካ በአድማጭ ትካዜ ተመታች::

By   /   November 23, 2023  /   Comments Off on ቬሮኒካ በአድማጭ ትካዜ ተመታች::

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 36 Second

በምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት አማካይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜን አሜሪካን የመጣችው ድምጳዊት ቬሮኒካ አዳነ የመጀመሪያ የመድረክ ስራዋን በአትላንታ ጆርጂያ ማድረጓን ተከትሎ በስቴጅ ፕሮፎርማንስ (በመድረክ አቀራረብ ደካማነት ) ተከታዮቿን እና የሙዚቃ አስፍቃሪውን ማህበረሰብ ያለ ምንም ማስደሰት በትካዜ ቆመው በማየት ብቻ በሙሉ የሙዚቃ ኮንሰርት ፕሮግራሙ ላይ ውጤት ሳታመጣ በመቅረቷ ምክንያት በተመልካች ድርቅ መመታቷን ለማየት ችለናል፡፡

ከለሊቱ አንድ ሰአት የተጀመረው ይህ የሙዚቃ ዝግጅት በቀዳሚነት በድምሻዊ ሲሳይ የተጀመረው የማህሙድ ለስላሳ ዘፈኖች ህዝቡን አስደስቶ ቢዘልቅም ከዚያም ቀጥሎ ለ42 ደቂቃዎች መድረኩን በቬሮኒካ አዳነ ቢመራም በእያንዳንዱ የሙዚቃ ስራዎች ውስጥ ለ3 ደቂቃ ያህል ዘፍና ታዳሚዎች እባካችሁ “ጨፍሩልኝ ” ገና እንቀውጠዋለን” እያለች ከመጮህ ውጭ ወደ መድረክ ዝር ብሎ ለሙዚቃው ፍላጎትም ይሁን ለስራዋ ድምቀት ለማጀብ የሞከረም አልነበረም ፡፡ ከአርባ ሁለተናው ደቂቃ በኋላ የገባው ብዟየሁ ደምሴ ኝ የህዝቡን ስሜት በለስላሳው ዘፈን ጀምሮ መድረኩን እረግጦ ለመያዝ ሞክሯል ፡፡

ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በጋዜጠኝነት የተመረቀችው ቬሮኒካ የተማረችበትን ሙያ ወደ ጎን በመተው የአዝማሪውን አባቷን ስራ በመከተል ወደ ሙዚቃው አለም ብትቀላቀልም ሆኖም ግን በሙዚቃው ላይ በስቱዲዮ ከሚቀረጱት ውጭ በመድረክ ላይ ለምንም መድረክ የማትሆን ለማወቅ ችለናል ፡፡

በወቅቱ ማለዳ ታይምስ ካነጋገረቻቸው ተመልካቾች አንዱ የአትላንታ ነዋሪ የሆነው ደረጄ እንደገለጰው ከሆነ ፣ ለመሸታቤት ማማሟቂያ ካልሆነ ለእንደዚህ አይነት ትልቅ መድረክ ብቁም አይደለችም ሲል ገልጵአል ፡፡ የምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት እንደ አንድ የኢንተርቴይመንት ተቋም በትክክል መስራት የሚችል ከሆነ የድምጳውያኑን ብቃት በዩቲዩብ እና በሲዲ ብቻ ሰምቶ ወደ ሰሜን አሜሪካን ከሚያመጣ ይልቅ የመድረክ አያያዛቸውን እና የሙዚቃ ብቃታቸውን ባጣመረ ሁኔታ በሙያተኛ አስጠንቶ ወደ ሰሜን አሜሪካ ቢያመጣቸው ማህበረሰቡንም የማያስቆታ ይሆናል ሲሉም የተደመጡ ሰዎች አሉ ፡፡

ወይዘሮ ማርታ የተባሉ ወይዘሮንም ማለዳ ታይምስ እንደአናገረች ከሆነ እኛ የማንም መጣያዎች ወይንም መሞከሪያዎች አይደለንም ጊዜ እና ገንዘባችንን እንፈልገዋለን ፣ ማንኛውም ፕሮሞተር እንዲህ አይነት ዘፋኞች በዩቲዩብ ብቻ ስለታወቁ ወደ ሙዚቃው አለም ቀላቅሎ ትልቅ ስም መስጠቱ ተገቢ አይደለም ሲሉ አስተያየታቸውን ለግሰውናል ፡፡

በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ የብዟየሁ ደምሴ የሙዚቃ ስራ ባይታከልበት ኖሮ ምናልባትም ህዝቡን ይበልጥ ያስቆጣ እንደነበርም ለመረዳት ችለናል፡፡

በሰሜን አሜሪካ የሚካሄደው የቬሮኒካ አዳነ የሙዚቃ ስራ ጥላ ያጠላበት ሲሆን ምናልባትም በየትኛውም ስቴት ቬሮኒካን ብቻዋን ሊያሰሯት ከሞከሩ የመውደቃቸው ስሜት ሰፋ ያለ ሲሆን ስም እና ዝና ከሙያው ጋር ልምድን ያካበቱ ዘፋኞችን ኝ አካተው ከያዙ ምናልባት ሊተርፉ ይችላሉ ብለን እናምናለን ፡፡

ማለዳ ታይምስ ሚዲያ ግሩፕ

You need to add a widget, row, or prebuilt layout before you’ll see anything here. 🙂

Happy
Happy
100 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 1 year ago on November 23, 2023
  • By:
  • Last Modified: December 11, 2023 @ 12:28 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar