በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ውስጥ የቤት ለቤት ፍተሻ በካዛንችዝ አካባቢ መጀመሩን የከተማው ነዋሪዎች ለማለዳ ሚዲያ ገልጸዋል ።
በከተማዋ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎች በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ከመሆናቸው የተነሳ የቤት ለቤት ውስጥ ፍተሻው በመንግስት ፓርላማ ያልተወሰነበት እና ህገወጥ ከመሆኑም ባሻገር ቀለሙ ያልጣማቸውንም ዜጋ በለሊት እያፈኑ መውሰድ መጀመራቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጠዋል ።
የከተማው ነዋሪዎች ለማለዳ ሚዲያ እንደገለጹት ከሆነ በአብይ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ የሃገሪቱ ኑሮጣሪያ ከመንካቱም ባሻገር ህዝብ እራሱን ማስተዳደር በማይችልበት ሁኔታ ውስጥ እየኖረ መሆኑን ቢገልጹም ፣ ከኑሮው በላይ የመንግስት ደህንነቶች እና የኦሮሞ ወጣቶች በአዲስ አበባ የቤት ለቤት አሰሳ መጀመራቸው የህዝቡን ኑሮ በጭንቀት ውስጥ እንደከተተው ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥም ይሁን በሌሎች ክልሎች እየተደረገ ያለው አፈና ከመጠን ያለፈ እና ህገወጥ ቢሆንም ህዝብ መንግስትን ከጠላ እና ከተነሳበት ህዝብን ማሸነፍ አይችልም ሲሉ ተናግረዋል ። በዚህም ምክንያት መንግስት ከህዝብ ጋር መስራት የማይችል ከሆነ እና የህዝብን መብት የማይጠብቅ ከሆነ በቀጣይ ህዝብም በአካባቢው መደራጀት እንደሚችል እና ጠላቱን ሊያጠፋ የመነሳት አቋም እንዳለው ገልጠዋል።
በሌላ በኩል ከደብረ ብርሃን በደረሰን መረጃ መሰረት በሰሜንሸዋዞን በአጠቃላይ የኢንተርኔት አገልግሎትምከጠፋ ሆነ የስልክ አገልግሎት በከፊል እንዲሰራ መደረጉ አግባብ አይደለም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ብቻ ሙሉ በሙሉ ኢንተርኔት ቢያገኙም ከዚያ ውጭ ያሉት ማናቸውም የግል ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች የኔትወርክ አገልግሎታቸው ከተቋረጠ ከስድስት ወራት በላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
መንግስት በሰሜን ሸዋ ህዝብ ላይ ግድያን በአሸባሪው ሸኔ በኩል ከፈጸመጊዜ ጀምሮ የአማራ ክልል በአፈና ውስጥ እንደአለ እና ሰላም የሌለው ክልል መሆኑን ገልጸዋል ።
ከሰሜን ሸዋ ወደ አዲስ አበባ መግባት ያልቻለው የአማራ ማህበረሰብ በፍቼ አካባቢ ከባድ ስቃይ እየደረሰበት ወደ መጣበት እየተመለሰ እንደሆነ ተገልጧል ።
Average Rating