www.maledatimes.com ጠቅላይ ሚንስትሩ ጦርነት ናፋቂ እና አረመኔ እንደሆኑ አቶ ታዬ ደንደአ ተናገሩ (ከስልጣንም ተነሱ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  ኣማርኛ  >  Current Article

ጠቅላይ ሚንስትሩ ጦርነት ናፋቂ እና አረመኔ እንደሆኑ አቶ ታዬ ደንደአ ተናገሩ (ከስልጣንም ተነሱ)

By   /   December 11, 2023  /   Comments Off on ጠቅላይ ሚንስትሩ ጦርነት ናፋቂ እና አረመኔ እንደሆኑ አቶ ታዬ ደንደአ ተናገሩ (ከስልጣንም ተነሱ)

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 37 Second

አቶ ታዬ ደንደአ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሥልጣናቸው የተሰናበቱት በአገሪቱ ያለው ጦርነት እንዲቆም ጥሪ በማቅረባቸው እንጂ ሌላ ምክንያት እንደሌለ ለቢቢሲ ተናገሩ።

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት አቶ ታዬ ይህንን የገለጹት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተፈረመ ደብዳቤ ከሥልጣን መነሳታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ይፋ ካደረጉ በኋላ ነው።

“ስለእርቅ ስለተናገርኩ ጦርነት ይቁም ስላልኩ እንጂ ሌላ ምክንያት የለም” በማለት ለቢቢሲ የገለጹት አቶ ታዬ፣ “በጦርነቱ ጊዜ ጦርነቱን ስደግፍ፣ ሲያበረታቱኝ ነበር። ሕዝቡ ይታረቅ ስንል ነው ያመማቸው። ጠርተው አላናገሩኝም። በአካል አልተገናኘንም” ሲሉ ምክንያት ያሉትን ተናግረዋል።

አቶ ታዬ በተረጋተጠ የፌስቡክ ገጻቸው ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተጻፈላቸውን የስንበት ደብዳቤ አያይዘው እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩን አምነው እንደተከተሏቸው እና በቃላቸው አለመገኘታቸውን ጠንከር ያሉ ቃላትን አስፍረዋል።

ስንብታቸውን በተመለከተ በፌስቡክ ላይ ያሰፈሩትን ጠንካራ ትችት በተመለከተ የተጠየቁት አቶ ታዬ “ይሄ እውነት ነው። ለሰው አያዝኑም። የሰው ልጅ ሞቶ አውሬ እየበላው ስለ ፓርክ ያወራሉ። ሰው የሚበላው አጥቶ እየሞተ በብዙ ገንዘብ ቤተ መንግሥት ያስገነባሉ” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ወቅሰዋል።

“የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር ዕሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት። አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰው ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ” ሲሉ በገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

በሕግ ሊያስጠይቃቸው የሚችል ነገር ይኖር እንደሆነ በቢቢሲ የተጠየቁት አቶ ታዬ ለዚህ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቅሰው ነገር ግን ይህ የሚሆንበት ዕድል እንደሌለ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።

“ይህ [በሕግ መጠየቅ] ምን ችግር አለው ታዲያ። ነገር ግን ሕግ የታለና በሕግ ይጠይቁኛል። ከጠየቁኝ ደግሞ ዝግጁ ነኝ።”

የመንግሥት እና የገዢው ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሆነው በጠንካራ ትችታቸው የሚታወቁት አቶ ታዬ ሰሞኑን በተከታታይ የሰነዘሯቸው አስተያያቶች ለስንብታቸው ምክንያት ይሆናል ብለው አያምኑም።

“ከዚህ ጋር የሚገናኝ አይመስለኝም። ከፓርቲያችን መርሆች ውስጥ ነጻነት አንዱ ነው። ከዚህ መርህ በተቃራኒ መቆም ተገቢ አይደለም። እኔ ስናገር የነበረው ይህንን መርህ መሠረት በማድረግ ነው” ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፊርማ ለአቶ ታዬ በተጻፈው ባለሦስት መስመር የስንብት ደብዳቤ ላይ የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመስግነው ከዛሬ ታኅሣሥ 1/2016 ዓ. ም. ጀምሮ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን አመልክቷል።

ከመስከረም 2014 ዓ. ም. ጀምሮ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ የነበሩት አቶ ታዬ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) አባል ሲሆኑ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እና በመገናኛ ብዙኃን ላይ በሚሰጡት አስተያየት የፌደራሉን መንግሥት እና የኦሮሚያ ክልልን በይፋ በመተቸት ይታወቃሉ።

ሰሜን ሸዋ የኩዩ ወረዳ እና አካባቢ ሕዝብን በመወከል የኦሮሚያ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታዬ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሚመራው ገዢው የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ናቸው።

ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ

የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት:: አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ:: እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር:: ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ:: ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ:: ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ::

እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል!

Kabajamoo Muummicha Ministeeraa Abiyyi Ahimadiif

Yaada Ida’amuu dubbattee fi barreessite amanee isin hordofe. Dhawaata garuu nama waan dubbatu hin jiraanne qofa otoo hin taane cubbamaa dhiiga namaatiin taphatu ta’uu keessanin hubadhe. Gaafan dhugaa sehee waraana bilaasha maqaa walabummaa biyyaatiin bantan, isa Itoophiyaanota wal-nyaachise, fi diinagdee biyyaa kuffise gegeessaa turtan deeggaretti na faarsaa turtan. Hardha gaafan dubbii argee gara nagaa goruun wal-ajjeechaan obboleeyyanii haa dhaabatu jennaan aangoo narraa fudhattan. Otoon shira Oromoo Oromoodhaan balleessuu fi obboleeyyan isaatiin walitti buusuuf kaatan argaa callisuu dhabuu kootii baayyeen gammada. Turtii waliin qabaannef galatoomaa!

Hagan jirutti qabsoon nagaa fi obbolummaa ummataatiif godhu itti fufa! 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 1 year ago on December 11, 2023
  • By:
  • Last Modified: December 11, 2023 @ 12:40 pm
  • Filed Under: ኣማርኛ

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar