0
0
Read Time:41 Second
በአሁኑ ሰአት በደረሰን መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሰራዊት በሰሜንሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ እና በገምዛ ወረዳዎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እየፈሸመባቸው እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጠዋል ፡፡
ከማጀቴ ጀምሮ ካራቆሬ ፣ እና አጣዬ አካባቢ ያሉትን ቦታዎች ካለፈው አራት አመታት ጀምሮ በኦሮሞው ሃይል ትቃት ሲደርስባቸው እንደነበር የሚታወስ ቢሆንም ከውስጥ ባገኘነው መረጃ መሰረት ጥቃቱ በመንግስት የታገዘ እንደነበር ምንጮቻችን ጠቅሰዋል፡፡
ዛሬም በአካባቢው ላይ የሚደረገው ጥቃት በመንግስት ትእዛዝ የተደረገ ቢሆንም ፋኖን እናጠቃለን በማለት ወደ ህዝቡ ጥቃት በመሰንዘራቸው ሳቢያ ፣ የአካባቢው ነዋሪው ህዝብም ምላሽ ለመስጠት ጥቃት መፈሸሙን ተናግረዋል ፡፡ ሆኖም ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ጥቃት የተነሳ ለጦርነትም ሆነ ለምንም ዝግጁ አይደለንም እራሳችን ካሳለፍነው መከራ ለማገገም እየሞከርን ነበር ሆኖም መንግስት ሆን ብሎ ህዝባችንን ገደለው ፣ አዳከመንም በማለት የጥቃቱን ሰፊነት ነዋሪዎች ለማለዳ ሚዲያ አብራርተዋል፡፡
ውጊያ ከፋኖ ጋር ነው እያሉ በእየ ህብረተሰቡ ቤት በመግባት ገበሬዎችን እየገደሉ ነው በማለትም የተናገሩ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት ህዝብን ይጠብቃል እንጅ ህዝብን ያሸብራል ብለን አንጠብቅም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
Wondering where the comments are? We encourage you to use the share buttons below and start the conversation on your own!
- Click to email a link to a friend (Opens in new window)
- Click to share on Facebook (Opens in new window)
- Click to share on Twitter (Opens in new window)
- Click to share on LinkedIn (Opens in new window)
- Click to share on Pinterest (Opens in new window)
- Click to share on Tumblr (Opens in new window)
- Click to print (Opens in new window)
Average Rating