www.maledatimes.com ♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

By   /   January 16, 2024  /   Comments Off on ♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 0 Second

#Ethiopia | ዛሬ ጥር 7ቀን 2016 ዓ.ም. ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ፍርድ ቤቱ በዛሬውም ዕለተ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ጉዳይ ከመታየቱ በፊት፤ “የማቀርበው አቤቱታ አለኝ” በማለት ለችሎቱ አነጋጋሪ እና ለዕለቱ ዳኛች ያልጠበቁት አቤቱታ አለኝ ፤ በማለት ጥያቄ አቅርቧል ።ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ፤ ችሎቱ ስለአቤቱታው ምንነት ጠይቆታል፡፡

ጋዜጠኛውም “የግራ ዳኛ የሆኑት አቶ መሐመድ አሕመድ ትክክለኛ ፍትሕ ይሰጣሉ ብዬ ስለማላምን በዚህ ጉዳይ ከችሎት እንዲነሱልኝ ስለምፈልግ ነው፤” ሲል መልሷል፡፡

ይህን ጊዜም የመሃል ዳኛው እና የቀኝ ዳኛው ለአፍታ ከተማከሩ በኋላ፣ አቤቱታውን በጽሑፍ እንዲያቀርብ ሲፈቅዱለት፤ ተመሰገን “በእዚህ ችሎት በርካታ ጋዜጠኞች ስላሉ አቤቱታዬን በንባብ እንዳሰማ ሊፈቀድልኝ ይገባል፤” ሲል ጠይቋል፡፡

ዳኞቹ እንደገና በለሆሳስ ከመከሩ በኋላ ሃሳቡን አሳጥሮ እንዲያቀረብ ፈቅደዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝም በጽሑፍ ያዘጋጀውን አቤቱታ ለችሎቱና ለታዳሚው እንደሚከተለው አንብቧል፡-

“ዐቃቤ ሕግ ጥቅምት 1/2015 ዓ.ም ባቀረበው የይግባኝ ቅሬታ 2ኛ ክስን በሚመለከት 3ኛ እና 4ኛ ፍሬ ነገሮች፤ እንዲሁም 3ኛ ክስን የይግባኝ ቅሬታ ያላቀረበበት መሆኑን ጠቅሶ ወደፊት ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ውጤቱን ተመልክቶ የይግባኝ ቅሬታ እንደሚያቀርብበት በይግባኝ ማመልከቻው ላይ በግልጽ አመላክቶ እያለ፣ ታህሳስ 17/2015 ዓ.ም መልስ ሰጪን ‹ያስቀርባል› በሚል ትዕዛዝ ከሰጡት ዳኞች መካከል አቶ መሐመድ አሕመድ የሚገኙበት መሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡ በችሎቱ የተሰጠው ትዕዛዝም ዐቃቤ ሕግ በ2ኛ ክስ ቅሬታ ያላቀረበባቸውን 3ኛ እና 4ኛ ፍሬ ነገሮችን በመጨመር፤ እንዲሁም 3ኛ ክስን በማካተት ‹በ1ኛ እና 2ኛ ክሶች መከላከል ሳያስፈልገው በነፃ እንዲሰናበት፣ 3ኛ ክስን በሚመለከት ክስ የቀረበበት ድንጋጌ ወደ ጥላቻ ንግግር ወይም የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከለከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1185/2012 አንቀጽ 4 በመለወጥ እንዲከላከል በአብላጫ ድምጽ የተሰጠውን ብይን፤ እንዲሁም የተጠቀሰውን አዋጅ ለጉዳዩ ያለውን አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑን ስለታመነበት መልስ ሰጪ ‹ይቅረብ› ብለናል በሚል ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡”

ጋዜጠኛ ተመስገን ለችሎቱ እንዳመለከተው፣ ይህ ትዕዛዝ ዐቃቤ ሕግ በይግባኝ አቤቱታው ከጠየቀው ዳኝነት በማለፍ የተሰጠ እንደሆነ በአጽንኦት አሳስቧል፡፡

ጋዜጠኛው ሃሳቡን ሲጠቀልል ፤ “ዳኛ መሀመድ በዚህ ጉዳይ ከችሎት ሳይነሱ ‹ይቀጥሉ› ቢባል፣ ጉዳዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው እንደመሆኑ መጠን በመዝገቡ ላይ ትክክለኛ ፍትሕ ይሰጣሉ ብዬ የማላምን እና ወደፊትም የሚሰጠው ፍርድ ነፃና ገለልተኛ ይሆናል ብዬ ስለማላምን በአዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀጽ 33/1/ሠ/ መሠረት የግራ ዳኛ የሆኑት አቶ መሐመድ አሕመድ በዚህ ጉዳይ ከችሎቱ እንዲነሱልኝ እጠይቃለሁ፤” ሲል አቤቱታውን ደምድሟል፡፡

የጋዜጠኛውን አቤቱታ ያዳመጠው ችሎቱም “ዳኛው ይነሱ ወይም አይነሱ” የሚለውን ለመወሰን እና በዋናው ክስ ላይ ጋዜጠኛው የሚያቀርበውን መልስ ለመቀበል ለጥር 28/2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ዛሬ በዋለው በጋዜጠኛ ተመስገን ዳሳለኝ ችሎት ፤ ጋዜጠኛች እና የሰብዓዊ መብት ተቋማት ተጠሪዎች እና የጋዜጠኛ ተመስገን አድናቂዎች በችሎቱ ታዳሚ ሆኗል ።

በመጨረሻም፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመላው አገሪቱ የሚቀርቡ የይግባኝ ቅሬታዎችን የሚያይ ከመሆኑ አኳያ፣ ጥያቄ የሚነሳባቸው ዳኞች እንዲሰየሙ ማድረግ የፍትሕ ሥርዓቱን ተአማኒነት አደጋ ላይ ሊጥለው እንደሚችል በችሎቱ ከነበሩ ታዳሚዎች ለዚህ ዜና ዘገባ አስተያየታቸውን ገልጸዋል፡፡

በይድነቃቸው ከበደ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Ethiopia’s Media Under Siege Amid Escalating Conflict in Amhara

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar