www.maledatimes.com ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ተመልሳ ልትመጣ ነው… “የት ሄደሽ ነበር…?” አለ ፋንቱ! | አቤ ቶኪቻው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ተመልሳ ልትመጣ ነው… “የት ሄደሽ ነበር…?” አለ ፋንቱ! | አቤ ቶኪቻው

By   /   November 21, 2012  /   Comments Off on ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ተመልሳ ልትመጣ ነው… “የት ሄደሽ ነበር…?” አለ ፋንቱ! | አቤ ቶኪቻው

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 10 Second
በርዕሱ ጀመር የተደረገው የጋሽ ፋንቱ ማንዶዬ ዜማ ሲቀጥል

“የት ሄደሽ ነበር?”

“አምባ አምባ ተለኬ አምባ…”

“ምነው ዘገየሽ?”

ቢይዘኝ ቢይዘኝ ጎልማሳ…”

እያለ ይቀጥላል።

ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ ጎልማሳም ሳይዘው ማተሚያ ቤትም ሳይዘው መንግስትም ሳይዘው እስከዛሬ የት ነበር!? ብለን እንጠይቃለን!

ከሶስት ነው አራት ወር በፊት ለካስ ቻናል ሆዬ ለሁለት አመታት ያክል የመንግስት ግብር አይከፍልም ነበርና “አሁንስ አበዛከው” ተብሎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ ለአንድ ቀንም በእስር ቤት አደረ። (መሰለኝ… ነው ወይስ በለሌት እኒያ ዘመዱ አስፈቱት) ብቻ ግን እርሱም ሆነ የማስታወቂያ ድርጅቱ ባለይዞታ ይሆኑት ባለቤቱ እስር ቤቷን ቀመስ አድርገዋት ወጡ።

ጋሽ ሳምሶንም በዚህ ጉዳይ ቶቆጣ! ኢትዮ ቻናል ጋዜጣ መንግስትን አቅፈው ደግፈው ከያዙት ጋዜጦች አንዷ ናት። ታድያ መንግስትን ደግፌ ይዤ እንዴት ግብር ክፈል እባላለሁ ብሎ አኮረፈ! አኮረፈና እንደውም ጋዜጣዋን አላሳትምም ብሎ ጥግ ላይ ቁጭ አለ።

ፍትህ እና ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣዎች ግብርም የማተሚያ ቤት ክፍያም ሳያጓድሉ አትታተሙም ተብለው አንዴ መልካቸውን አንዴ ስማቸውን እየቀያየሩ ለመውጣት ተገደዋል።

ኢትዮ ቻናል ግን ለምን ግብር ክፈል ተባልኩ ተብሎ አኮረፈ ኩርፊያው ሲያልቅም ተመልሶ መጣ “እረኛ ቢያኮርፍ ቁርሱ እራት ይሆነዋል” ያለው ማን ነበር…

ወዳጅ ተስፋለም በፌስቡኩ ላይ “ኢትዮ ቻናል ልትመጣ ነው” ብሎ በለጠፈ ጊዜ ታሪከኛው ዘላለምም አለው “ደሞ መጣች ልታስቀን!” እኛም አልን… ሃሃ…!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on November 21, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 21, 2012 @ 4:37 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar