www.maledatimes.com ተናካሹ ጥርስ የሌለው አንበሳ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ተናካሹ ጥርስ የሌለው አንበሳ

By   /   January 28, 2025  /   No Comments

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 48 Second

በሰሜን አሜሪካን አካባቢ የተነሳው ወጀብ የባህር ጥልቀትን ይዞ የሚጎዘው እና ምንም አይነት ስነ ምግባር እና የህግ ስርአትም ሆነ ብልሃት ያልታከለበት የአትላንታው የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ በአትላንታ የእርስ በርስ ግጭት ነው::

ከሃገራችን ወቅታዊ ፖለቲካ በማይሻል እና በተጋደደ ሂደት እራሱን ይዞ እየተጏዘ ያለ ቢሆንም አመራር እና አስተዳደሮች የህፃን ልጅ ጨዋታ ይዘው የስድብ ቅብብሎሽ ድብድብ ቀረሽ ስድቦችን እያስተናገደ ቢሆንም ምንም አይነት መፍትሔ ይዞ ሊመጣ ያልቻለ መሆኑን ለመረዳት ችለናል::

ከተቋቋመበት ዘመን ጀምሮ በፌደራል መንግስትም ሆነ በግል የሒሳብ አያያዝ ባለሙያዎች (አካውንታንቶች) ኦዲት ተደርጎ የማያውቀው እና የወጣው የገባው ሁሉ ኮሚኒቲውን ተጠቅመውበት የሚያልፉበት ሲሆን አንዳንድ የቦርድ አባላቶች ደግሞ የቤተሰብ ንብረት ይመስል ባል ከ ሚስት ጋር እየተፈራረቁ የሚመሩበት ድርጅት በመሆኑ ወደ ውድቀት እየዳረጉት ስለመሆኑ ለማወት ተችሏል ::

አንዳንድ የውስጥ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ደግሞ  ኮሚኒቲው የተለያዩ አራት የባንክ አካውንቶች ያሉት እንደሆነ እና አሁን ባለው አመራሮችም ሆነ በቀድሞዎቹ የተዋረድ ስራ ላይ ምንም አይነት የሂሳብ ዝውውር የማይደረግበት ሲሆን :  የሰሞንኛው ማእበልም ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ያለ አግባብ ገንዘብን ለግል ጥቅም በማዋል በሚል ክስ የኮሚኒቲው ኦዲት ቁጥጥር ኮሚቴ  የባንክአካውንታቸው ኦዲት ይደረግ ብለው ጥያቄ ቢያቀርቡም ምንም አይነት ምላሽ ባለመስጠታቸው ምክንያት ለሁለት ጎራ ለይተው መናከስ ቢጀምሩም  ምንም አይነት እልባት አላገኙም ::

አዲሱ አመራር ሥልጣኑን ሲረከብ ኦዲት ሳያስደርግ የተቀበለ ቢሆንም አሁን ያለው የቁጥትር ኮሚቴ ኦዲት አያደርገኝም የሚል እምቢታን አሳይቷል :: ግን  ለምን ?

ሦስተኛው ቡድን ደግሞ ከዚህ ቀደም በአመራር  ደረጃ ላይ የነበሩ  አባላቶች በሁሉም ላይ ጥርሳቸውን አሹለው እነርሱም ጥርስ የሌለው አንበሳ ለመሆን በቅተዋል ::

በተለይም የኮሚኒቲው የቦርድ አባል የነበረው እና ኮሚኒቲውን ሆነ ማህበረሰቡን ለመከፋፈል ትልቁን ድርሻ ከሚወጡት መካከል አቶ መርዕድ አለማየሁ የሚባሉት ግለሰብ አንዱ መሆናቸውን የኮሚኒቲው አባላቶች ለማለዳ ሚዲያ አድርሰዋል::

ሰርተው የማያሰሩ ሰዎችን ያለ ምግባራቸው ምግባርን የሚሰጡ አባላቶች ውስጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ናቸው ሲሉምአክለው ተናግረዋል በዚህም ላይ አክለው ሲገልፁ እኝሁ ግለሰብ ጊዜአቸው አብቅቶ ከስልጣን መንበራቸው ቢወርዱም በምትካቸው ባለቤታቸውን ተክተው ወርደዋል ይህ ደግሞ ለኮሚኒቲያችን አግባብ አይደለም ብለው ቅሬታቸውን ተናገዋል:: ይህም ችልታን የሚያሰጥ አይደለም::

የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ በአትላንታ በሁለት የህግ መተዳደሪያ  ያውም የአትላንታ ማህበረሰብ በማያውቀው እና ባላፀደቀው ህገ ደንብ ለግል ጥቅማቸው በሚበጅ መልኩ እያቀያየሩ እየተጠቀሙት ነው ሲሉም ቅሬታቸውን አሰምተዋል::

 

በሌላም በኩል  ኮሚኒቲው በቅርቡ ለሽምግልና ጥሪውን ሲያቀርብ የኮሚኒቲ በአባልነት የተመዘገቡትን ብቻ ነው የምናስተናግደው ብለው ጥሪ ማቅረባቸው ሌላው ሰፊውን ቅሬታ አስነስቷል ::

ምክንያቱም “የኢትዮጵያን ማህበረሰብ በአትላንታ ብለው ስያሜ በተሰጠው ትልቅ አገር አቅፍ ስም ላይ ማንኛውንም ማህበረሰብ አካታች ሳይሆን እና ከ100 እስከ  ከ150 ሽህ በላይ ኢትዮጵያውያን  ይኖርበታል ተብሎ የሚታሰበውን የጆርጂያን ስቴት ኢትዮጵያውያን አባላትን ልብ ከመስበሩም በላይ  ሕዝብን ከመንግስት እኩል  በዘር በመጡበት የቦታ እናክልል ስፍራ በመከፋፈል ሌሎችንዘሮች አካታች ሳይሆን ኢትዮጵያዊነት  አይንፀባረቅም  ይህም መንግስት እንደሚያደርገው የጅምላ ግድያ ጨፍልቆ እንደመግደል ነው ሲሉም ማህበበሰቡ ለማለዳ ሚዲያ ገልጠዋል::

 

ጥርስ የሌለው አንበሳ ሊበላን ነው እባካችሁ በህብረት የህዝባችንን ንብረት እናድንም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል:: ይቀጥላል ……

 

ከአስተያየቶቹ ጥቂቶቹ  የሚ  ተገኘ

Dear Ethiopian Comunity leaders

I hope this message finds you well. As we prepare for the upcoming meeting, we wanted to kindly request a copy of the agenda. Having an overview of the topics to be discussed will help us come prepared and ensure that we can engage effectively during the discussion.

Transparency is important to us, and knowing the agenda in advance will allow us to ask thoughtful questions and contribute meaningfully to the conversation.

Thank you for your understanding and support. I look forward to hearing from you.

ውድ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ መሪዎች

ይህ መልእክት በሰላም እንደሚያገኛቹ

 ተስፋ አደርጋለሁ። ለመጪው ስብሰባ ስንዘጋጅ የአጀንዳውን ቅጂ በትህትና ለመጠየቅ ፈለግሁ። የምንወያይባቸውን ርእሶች አጠቃላይ እይታ ማግኘታችን ተዘጋጅተን እንድንመጣ እና በውይይት ወቅት ውጤታማ ተሳትፎ ማድረግ እንድንችል ይረዳናል።

ግልጽነት ለእኛ አስፈላጊ ነው፣ እና አጀንዳውን አስቀድመን ማወቃችን የታሰቡ ጥያቄዎችን እንድንጠይቅ እና ለውይይቱ ትርጉም ያለው አስተዋፅኦ እንድናደርግ ያስችለናል።

ስለ መረዳትዎ እና ድጋፍዎ እናመሰግናለን። ከእርስዎ ለመስማት በጉጉት እንጠብቃለን።

 

 

አቶ ለአከ

 

Damage control: For the past four weeks  I have listened interviews by former community officials, and other concerned members of the community’s, so far none of them mentioned the root of the problem. 

Moving forward. 1ኛ: የስብሰባው እልት ሰፋ ያለ ጊዜ ለህብረይተሰቡ እንዲሰጥ:  በበስነስርዓት ታዳሚው ሀሳቡንብ መግለፅ እኒዲቾል ወይም እንትችል: : ስብሳቢው dictate ማድረግ የለበትም: 2ኛ: የህገ ደንቡን ረቂቅ የሚፈትሽ መጨመር ወይም ቀነስ ማሻሻል የሚያ ደርጉ  ከኮሚኒቲው ዓባላት  ውስጥ ማዋቀርና የመጨረሻውን ረቂቅ ለህግ ባለሙያ ማሳየትና the final version should be posted at the community Webb sight so member’s can read it  and adopt the by law. During members meeting. በማህሩ ውስጥ ችግሮች ስለነበሩ  ነው  ለዚህ  ብጥብጥ ክፍፍል የበቃነው:በጣም የሚገርመው በሶሻል ሚዲያ በመቅረብ ህብርተሰቡን በ volunteer ማገልገል የሚፈልግ የለም ማለት ከእውነት የራቀ  ነው how do you expect to find volunteers, when you bark like a mad dog, when individuals ask too volunteer. I have seen for several years few individuals want be the mover and the shakers. 

Finally, for a better community institution, we need fact finding, why, when, how, where and who, to fresh start.

 

የተከበራችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ:

በቦርድ ሊቀንበራችን በተጠራው ህጋዊው ጀንዋሪ 26/2025 አስቸኳይ ስብሰባ እሁድ ከቀኑ 3pm ላይ ስለመገኘት!!!

 

እንደምን ዋላችሁ::

በትክክለኛ መሠረት ላይ የቆመች እውነት ምንጊዜም በውሸት ወጀብና ንፋስ አትነቀልም::

በአሁኑ ሠዓት   አንዳንድ የሚናፈሱ ከእውነት የራቁ ወሬዎች የተወሰናችሁትን ሊያደናግርና ግራ ሊያጋባ ይችላል:: ነገር ግን በእናንተው የበላይነትና ውሳኔ ሠጭነት እዲሁም ባለቤትነት የተመሠረተ የኮሚኒቲ ማህበር ስለሆነ ከእናንተ በላይ የሚሆን አንዳችም ችግር የለም ::

***ትልቁ ቁም ነገር በሚዲያ የተነገረውና የተባለው ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ መቸም ለእናንተ አንነግርም:: የሚነገረውንም ሣናጣራ : ሳንጠይቅ መቀበል እንደሌለብን ይህ የSocial Media ዘመን እስካሁን ሁላችንንም ያስተማረን ይመስለኛል:: ይህ ይጠፋችሗል ብየ በፍፁም አልገምትም::

** በአሁኑ ሠዓት ዓመታዊ የዕድርና የኮሚኒቲ ማህበራችንም ክፍያ እየተካሔደ ይገኛል:: ህሉም መደበኛ ሥራ በኮሚኒቲያችን እየተሠራ ይገኛል:: ብቅ እያላችሁ እውነተኛውን ትክክለኛውን ነገር ማግኘት ትችላላችሁ:: እገረመንገዳችሁንም ክፍያችሁን እንድታጠናቅቁ አደራ እንላለን::

በአመራሮች መካከል አለመግባባት ልዩነቶች የነበሩ ያሉ ወደፊትም የሚኖሩ ናቸው:: በመነጋገር በመመካከር ሁሉም ይፈታል :: በተለይም የእኛ ኮሚኒቲ ማህበር የበላይ አካል የሆነው የማህበሩ አባላት ጠቅላላ ጉባዔ ስለሚሆን በቀላሉ ተገናኝቶ እልባት ይሰጥበታል::ይህ ስለሆነም ሳንደናገር የሚባሉ አሉባልታዎችን ሳናጣራ  በመስማት እንዳንረበሽ አደራ እላለሁ:: 

ምጊዜም ከፍታና እድገት ሲመጣ ያንን ለማደናቀፍ የሚከሰቱ መሰናክሎች በሁሉም ይኖራል :: በግል ህይዎታችንም እንደሚያጋጥመን ሁሉ ማለት ነው::

አሁንም  ሁላችንም ትልቁን ዓላማና ግብ ከያዝን የኮሚኒቲያችንን እድገት ከተመኘንና በእሱ ላይ ካተኮርን ሁሉም ነገር ይስተካከላል:: ይፈታል: በእናንተ የበላይነት ውሳኔ መስመሩን ይይዛል::

 በጋራ በአንድነት የማንሻገረው አንዳችም ችግር የለም::

“A lie can travel halfway around the world while the truth is putting on its shoes.” – Mark

አመሰግናለሁ

ተክሌ ደመቀ የአሁኑ የኮሙኒቲው ዳይሬክተር

ዳሬክተር

ማለዳ ሚዲያ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

* Copy This Password *

* Type Or Paste Password Here *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በአስገድዶ መድፈር ተከሦ የነበረው ያሬድ ጌታቸው ታሰረ

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar