ኢትዮጵያዊው ያሬድ ጌታቸው መኮንን ከዚህ ቀደም በፈጸመውየወሲብ ጥቃት በኢሚግሬሽን ኤንድ ከስተምስ ኢንፎርስምነት (ICE) ተያዘ ።
በነጩ ቤተ መንግስት ይፋዊ ድረ ገፅ ፣ በኒው ኦርሊንስ ከተማ የአገሪቱ የስደተኞች እና የጉምሩክ ተቋም የሆነው ኢሚግሬሽን ኤንድ ከስተምስ ኢንፎርስምነት (አይስ) ባካሔደው አሰሳ ለህብረተሰቡ ከፍተኛ ስጋት ነው ያለውን ያሬድ ጌታቸው መኮንን የተባለውን ኢትዮጵያዊ አደገኛ የወሲብ ጥቃት ፈጻሚ እና አስገድዶ ደፋሪ ወንጀለኛን ባሳለፍነው አርብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
የ33 ዓመቱ ጐልማሳ ያሬድ ጌታቸው መኮንን ከስምንት ዓመት በፊት May 26 ቀን 2017 ዓ/ም ከለሊቱ 3፡15 AM አካባቢ በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ የ24 ዓመት ወጣት እያለ በታክሲ ሹፌርነት በሚያገለግልበት ወቅት፤ በዩ ጎዳና (U Street) አካባቢ ከወንድ የፍቅር ጓደኛዋ ጋር ስትዝናና ቆይታ በመጠጥ ስክራ የነበረች ወጣት፣ ጓደኛዋ በታክሲ ካሳፈራት በኋላ፣ ወደ ቤቷ በመሔድ በነበረችበት ወቅት፣ ከኋላ ወንበር ቁጭ እንዳለች ሀይለኛ እንቅልፍ ይወስዳታል።
ያሬድ ወደ ኋላ ወንበር በመሔድ እጅግ ሰክራ የነበራቸውን ወጣት አስገድዶ የግብረ ስጋ ግንኙነት እየፈፀመ ስትነቃ ማግኘቷን ገልፃ ፤ተሳፋሪዋ እየደፈራት መሆኑን ስታቅ ከታገለችው በኋላ፣ ወደፊት ወንበር ሔዶ መኪናውን መንዳት መቀጠሉና፣ እንዲያወርዳት ብትለምነው ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን በጊዜው ለፖሊስ በሰጠቸው ቃል ገልፃ ነበር። ያሬድ ተሳፋሪዋ ወደ አሌክሳንድሪያ፣ ቨርጂኒያ ለመሔድ መዳረሻዋ አድርጋ የተሳፈረች ቢሆንም፣ ወደ ሌላ አቅጣጫ ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ ይዟት ለመሔድ በሚነዳበት ወቅት፣ በአጠገቡ ሲሄድ የነበረ መኪና ተሳፋሪዋ ስትጮህ በመስማቱና፣ ለእርዳታ እጇን ስታውለበልብ በማየቱ ከታክሲው ፊት ለፊት መንገድ ዘግቶ በመቆም ወዲያው ለፖሊስ በመደወል ያሬድ እንዲያዝ አድርጓል።
ያሬድ የተሳፋሪዋን የእጅ ስልክ ለፖሊስ እንዳትደውልበት በማሰብ ነጥቆ ሰብሮ በመስኮት በኩል መወርወሩ የፖሊስ ሪፖርት ያመለክታል። ፖሊሶች በደረሱበት ወቅት ያሬድ ድርጊቱን እንዳልፈፀመ ገልፆ ፣ ወደ ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ ሊወስዳት ሲል እያለቀሰች እንዳስቸገረችው እና ፊቱን እንደ ቧጨረችው ገልጿል። በቨርጂኒያ ነዋሪ እንደሆነች የገለፀችው ተሳፋሪዋ፣ በሜሪላንድ ምንም የምታቀው ሰው አለመኖሩ እና ለምን ወደዛ ሊወስዳት እንዳሰበ እንደማታቅና፣ የያሬድ መኖሪያ ቤት ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ሜሪላንድ መሆኑን ፖሊስ አረጋግጧል።
በጊዜው ያሬድ በስፍራው በፖሊስ ቁጥጥር ከዋለ ስር በኋላ፣ በሁለተኛ ደረጃ የፆታ ጥቃት በማድረስ ክስ ተመስርቶበት፣ በአፈና እና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ተከሶ የነበረ ሲሆን፣ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የዘጠኝ አመት እስር ተፈርዶበት፣ ፍርዱን ጨርሶ ከእስር ተፈትቶ የነበረ ቢሆንም ፤ አደገኛ የፆታ ጥቃት ፈጻሚ ተብሎ ፋይሉ ውስጥ በህይወት ዘመኑ እንዲቀመጥ ተወስኖ ነበር።
ያሬድ ጌታቸው መኮንን ከዚህ ቀደም በፈጸመውየወሲብ ጥቃት ነው በኢሚግሬሽን ኤንድ ከስተምስ ኢንፎርስምነት (ICE) የተያዘው ።
በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሚገኙበት አሜሪካ ስደተኞች ላይ የተከፈተው ዘመቻ ብዙዎችን ያሰጋ ነው።
ዶናልድ ትራምፕ ወደ ዋይት ሐውስ በመመለሳቸው በአሜሪካ ያለፈቃድ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለማስወጣት የገቡትን ቃል ሊፈጽሙ ይችላሉ ሲሉም ብዙዎች ይፈራሉ።
መዝናኛ ሚዲያ፣ ዳንኤል ገብረማርያም፣
Daniel Gebremariam #meznagnia Meznagnia
Average Rating