www.maledatimes.com የላትቪያው (ልብወለድ መጽሐፍ) በገበያ ላይ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የላትቪያው (ልብወለድ መጽሐፍ) በገበያ ላይ

By   /   November 21, 2012  /   Comments Off on የላትቪያው (ልብወለድ መጽሐፍ) በገበያ ላይ

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 0 Second

በገበያ ላይ for more pls click here
መጽሐፉን በአራት መንገዶች በእጅዎ ማስገባት ይችላሉ፦
1ኛ. ይህንን ኢሜይል በመጠቀም:- yelatviaw@gmail.com
2ኛ. በአካባቢዎ ከሚገኝ የሀገር ልጅ ግሮሰሪ ጎራ በማለት
3ኛ. www.facebook.com ላይ Yelatviaw በማለት እና
4ኛ. ስልክ ቁጥር 682-503-3002 በመደወል
“የላትቪያው” በፍቅር፣ በፖለቲካ፣ በሰብአዊ መብቶችና በሀገራዊ እውነታዎች ዙሪያ የሚያውጠነጥን፤ 496 ገጾች ያሉት፣ ስፋትና ቁመቱ አነስ ተደርጎ ለየት ባለ ሁኔታ የታተመ ልብወለድ መጽሐፍ ነው። መጽሐፉ፤ የተለያየ አመለካከት ያላቸውን ግለሰቦች እይታ በጉልህ የሚያሳይ ከመሆኑ ባሻገር፤ አንባቢያንን እያስገረመ፣ እያሳዘነና እያስደሰተ ከገጽ ወደ ገጽ ይዞ የሚሄድ ነው።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት በሌለው አንድ የተማረ ወጣት ላይ የሚደርሰውን በደልና፣ ወጣቱም ዜጋዊ መብቱን ላለማስነካት በሚያደርገው ግላዊ ትግል ላይ መሰረት ተደርጎ የተጀመረ፣ ግን እየሰፋ ሄዶ፤ የኢሕአዴግን የደኅንነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ባህሪ፣ የተራ ገዳይ ስኳድ ሰዎችን ጽኑ ገዳይነት፣ እንዲሁም በዲፕሎማቲክ ዘርፍ ኢትዮጵያን ወክለው የሚገኙ ዲፕሎማቶች ምን እንደሚሰሩና የኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ምክንያት እየፈለጉ በኢትዮጵያ ሕዝብ ገንዘብ እንዴት እንደሚደንሱ ይተርካል።
በድብቅ ቀለበት ያሰረላትን እጮኛዋን ትታ፣ ልቧን የመነተፈውን አንድ ወጣት፣ የኢሕአዴግ መንግሥት የደህንነት መዋቅር ቢቀማት፤ የት እንዳደረሰውም ለማወቅና ለማስፈታት ያደረገችው ጥረት ያመጣባትን መዘዝ ችላው፣ እሱን ፍለጋ ከከተማ ከተማ የምትንከራተት አንዲት ቆጅዬ ወጣት ለፍቅር የምትከፍለውን ከፍተኛና በፍጹም ሊታመን የማይችል ዋጋን ያሳያል።
ልብወለድ ታሪኩ፤ አንባብያንን ወደ ትንሿ ሀግስበርገን፣ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ፎርጎትንላንድ፣ አዲስ አበባ፣ ቴልአቪቭ፣ ሃሮዲና፣ ናይሮቢ፣ ሞምባሳ፣ ናዝሬት፣ ኦታዋ፣ ሀዋሳ፣ ሞያሌ፣ ቀርሳ፣ ሞዬ እና ወደ ሌሎች ቦታዎችም በምናባቸው እንዲጓዙ ያስገድዳል።
የኢሕአዴግ መንግሥት፣ ዜጎችን ተራ በሆነ ነገር ሁሉ ሲያስመርራቸው፤ ዜጎችም በፋንታቸው በኢሕአዴግ መንግሥት ተማረው የሚመርጡትን ፖለካዊ መሥመር በማያሻማ መልኩ በጉልህ ያንጸባርቃል። “ፖለቲካ አናውቅም!” የሚሉ ዜጎችን “ፖለቲካ እናውቃለን!…..ፖለቲካ አሁን ገብቶናል!” እንዲሉ የሚያስገድዳቸው ምክንያት ምን እንደሆነ፤ ከፖለቲካ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ዜጎች በሌሎች ምክንያቶች እንዴት በኢሕአዴግ እንደሚነጩና በሰላም ከቤታቸው ወጥተው ሳይመለሱ እንደሚቀሩ የመጻፉ ታሪክ ይገልጻል።
ምስራቅ ሸዋ ውስጥ በሚገኝ አንድ ግድብ ላይ፣ ከሌላ ዓለም የመጡ ፍጡራን ሊያደርሱ ያቀዱትን አደጋ አስመልክቶ፤ የኢሕአዴግ መንግሥት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች፣ በውጭ ሀገርና በሀገር ቤት የሚገኙ ዜጎች እንዲሁም የጎረቤትና ወዳጅ ሀገራት፤ አፋጣኝ ምላሽ ምን እንደሆነ ያዩበታል። የኢሕአዴግ መንግሥት ለናዝሬት ቴክኒካል ኮሌጅ በኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት አማካሪነት የቀጠረው አንድ ጃፓናዊ፣ ናዝሬት ቴክኒካል ኮሌጅ ውስጥ ቁጭ ብሎ ቀጣሪው ኢሕአዴግን እንዴት እንደሚጫወትበት፣ ዋና ጽ/ቤቱ ናሚቢያ የሆነና ኢፐልፕ የተባለ የተቃዋሚ ድርጅት ዋና ሰላይ (የላትቪያው ኢንጂነር) ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ የኢሕአዴግን የደኅንነት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት መከራውን ሲያሳየውና ጨርቁን ሲያስጥለው ይደነቁበታል።
ይህ መጽሐፍ በአንባብያን ዘንድ የተለያየ ትርጓሜ ሊሰጠው ይችል ይሆናል። በመጽሐፉ አዘጋጅ ዓይን ግን፣ ከተራ የልብወለድ ታሪክነት ያለፈ ምንም ዓይነት ተልእኮና ምስጢር የለውም።
የመጽሐፉ ደራሲ ኢትዮጵያ ውስጥ በነበረበት ወቅት፣ የናዝራዊ ነጻ ጋዜጣ ሪፖርተርና ቀጥሎም የናዝሬት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነበር። ሁለቱ ነጻ ጋዜጦች የተመሰረቱት ከሀገሪቱ ዋና ከተማ ወጣ ብላ ለምትገኘው ለናዝሬት/አዳማ እና አካባቢዋ ድምጽ ሆነው ለማገልገል ነበር። ጋዜጣዎቹ ለሁለት ዓመት ለሚሆን ጊዜ ቆይተው፣ በአካባቢው በሚገኘው መንግሥትና የራሳቸው የሆነ የተለያየ ጥቅም ባላቸው ቡድኖችና ግለሰቦች ትጽእኖ ምክንያት ሕትመታቸውን ለማቋረጥ ተገደዋል። በስደት ዓለም፣ ደራሲው አልፎ አልፎ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ ጽሁፎቹን ዋና ዋና በሚባሉ የኢትዮጵያ ድረ ገጾችና ጋዜጦች ላይ ያስነብባል። ደራሲው በአሜሪካ የሚኖር ሲሆን “የላትቪያው” ልብወለድ መጽሐፉ ቀድሞ ለህትመት የበቃ እንጂ የመጀመሪያ ሥራው አይደለም።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on November 21, 2012
  • By:
  • Last Modified: November 21, 2012 @ 9:07 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar