www.maledatimes.com ይድረስ ለአርያም - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ይድረስ ለአርያም

By   /   March 20, 2013  /   Comments Off on ይድረስ ለአርያም

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 16 Second

የምፈራቸውን፡ ከውስጥም ይሁን ከውጭ የሚያስጨንቁኝን ድምፆች ምናል ባልሰማቸው?! ምናል የፆታየን፡ የወንድነቴን ያህል ብመላለስና ፍርሃትን ብቻ መፍራት ብለምድ? ኦህ ነፍሴ ምንኛ ባልተለመደ ሽንፈት ባልባዘንሽ ነበር፡፡ ይገርመኛል!! ላዋቂ ቀርቶ ለህፃናት ስጋት የማይፈጥረው የምኩራብ ደወል ባቃጨለ ቁጥር በታማኝነት መደንበሬ:: ውል ባለው ህይወት መገኘቴን ተዉት በምድሪቱ ላይ የመከሰቴ ሁነኛው ትርጉም ሳይገለጥልኝም ግን የደወሉ ጥሪ ለኔ ቢሆንስ ማለቱን ብቻ ይዥ እንደሞኙ ብላቴና በባዶ አለቃቅሳለሁ፡፡ ደግሞ እዛው ደጀሰላሙ ላይ ተደፍቼ አምላክ ፣ አማልክት፣ ፍጥረትና አለማቱ ሁሉ በጥልቅ ቀርቶ የአምሳያውን ያህል ሳትገለጡልኝ በፊት ሞትን አትጥሩብኝ አልሁ፤ (ለካንስ ተማፅኖየን ለብርሃናቱ ሁሉ ገዥ ያንደበቴን ድምፅ ከፍ በማድረግ ሳሰማ የምኩራቡ ዘበኛ ኤሎሄየን ሰምተው ሃዘኔን ሊጋሩ አብረውኝ በጸሎት ይተጉ ኖሯል!! እነሆም ደስ ተሰኝቼ ጌታየ ሆይ ስለተመረጡት ስትል በኔ በልጅህ ላይ ስላለህ አላማ አንድ ቃል ብትናገር ወደድሁ ስል ተማጥኘ በእንባ የረሰረሱ አይኖቼን ወደ አርያም መለስኳቸው )
እንዲህ ስል አሰብሁ ደግሞ ያ የሚጭንቀኝ የኔ የዘመናት ጥያቄ አንድ ብቻ ሳለ ዳሩ ግን እንደ ዝግባ ዛፍ በዝቶ መንፈሴን ጋርዶታል፤ በእውነት ያስቃችሁ እንደሁ አላውቅም ግን ለኔ የመደሰትን ያህል የከበደኝና ሰቀቀን ውስጥ የሚከተኝ ከባድ ሃዘንም ቢሆን አጣሁ እናም ሃሴትን ያህል ብርሃን በወጣትነት እፍታ ላይ እያሸረገድሁ “ጨለማ ነህ!” አልሁት፤ ቀጥሎም በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት መፈለጌን ይልቁንም በራሴ ላይ ያደረዉን ክፉ ተግዳሮትና ትምክህት አብዝቼ ጠላሁት ነገር ግን የሚያሳዝነው ይህንንም ማወቄ አሁንም በእናንተ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኜት እንጂ ተጨባጭ የህይወት ፍልስፍናየ አይደለም፡፡ (አሁን ቅዱስ መናፍስት ከሚያረብቡበት ስፍራ ሆኜ እኒያ መልካሙ ዘበኛ የለት ተግባራቸውን ሲፈጥሙ እያየሁ የነፋሱን ሽውታ ወዲህ ለብቻየ ሳደምጥ ፍርሃትና ለቀቅ የማለት ስሜት ባንድላይ ይፈራረቁብኝ ጀመር)
ምናለ የተሲዓት ድምፆች በመዓልት እንኳ ስለ አንድ ታማኝ ፈሪ ሲሉ የሚቆለፉ ገዳማዊ አንደበቶች ቢሆኑ!? እናም እንደ ፍጡር ደካማነቴን ማለት ሸክላ፡ ሸክላ ሰሪዉን እንደማይፈትን ሁሉ ሰው ሆኜ መገኜቴን ብቻ ተቀብየ መኖር በቻልኩና ከዋሻ ሰው ያልተለየ ቁዘማየን “ሃይ” ባልኩት፡፡ ስለምን እንደቶማሳዊያን “ካላየሁ አላምንም” ማለትን ትቼ ያላገኘውህ አምላኬ ሆይ ካመንኩ በኋላ እንዳይህ የእገዛህ መገኘት አልሆነልኝም??? “ይሁን!” ብቻ በሚል ዓለምን በህልው የገለጠ ታምራዊ ቃልህ እንዲሁ “ይሁን!” ብለህ ከፈታኝ ነፍሴ የኔንም ህይወት እባክህን መለኮት ሆይ አሳርፋት??? ባይሆን ግን የጌትነትህ እሳት እስኪለበልበኝ ምልክት ከሚሻ ትውልድ አንዱ ነኝና ደጀሰላምህ ላይ በነፍስ ጦርነት ተይዥ ታምርህን እጠብቃለሁ፡፡ እስከዛም መልስ ባጡ ፋይዳቢስ ጥያቄዎች ራሴን ስሸነግል የቀትር ፅሃይ ነባራዊ ልምዷን ልትከውን ወደ ውብ ጀምበር ትቀየርና ዘበኛውም መጥተው አምላክ ሆይ ከቤትህ ያሰናብቱኛል፡፡ እና ያኔ ከንቱ ሰው መሆን ይዞኝ ለስጋየ ማደሪያ ስርቻየን ሳፈላልግ ቸርነትህን ብዘነጋ ሃጥያት አይሁንብኝ
(ዶሮ ማነቂያ አካባቢ ባሳር ካገኘኋት አንድ ብር ከሃምሳ ሳንቲም ምቹ መደቤ ላይ ሆኘ ቀን ምኩራቡ ውስጥ ሳለሁ ጀምሮ ሳሰላስለው ከነበረው ሃሳብ ጋ እንደተለጠፍኩ እንቅልፌን መጠባበቅ ቀጠልሁ) በእምነት ብቻ ላይህ የምሻ እግዚአብሄር ሆይ ከቶ ለምን ይሆን ላማልክቱ እንኳ በማይፈታ መለኮታዊ ውዥንብር የነፍሴን ሹልዳ ታግለህ ያስነከስካት??? ይኄው በዚህ ድርጊትህ ደስታውን የሚጸየፍ ቆዛሚ ፈጥረሃልና ማርከሻውን መና መላእክቱን አዘህ ታወርሰኝ ዘንድ አቤት አልኩህ! ቅንጣት ምላሽ በሌለበት በዚያ እንኳ ማመን እንዲኖር አውቃለሁ ነገር ግን የዚህ ዓለም እውነት ከሚያዝ እይታ ተነስቶ ስለማመን ቢያስተምረኝ ጊዜ ሲኦልን ፈርቼ ሳይሆን ፍቅርህን አውቄ ብከተልህ ተመኘሁ፡፡ አምላኬ ሆይ ዛሬም እንደትናንቱ የምፈልገውን ሳይሆን የሚጠቅመኝን ብቻ አንተው በፍቃድህ ትሰጠኝ ዘንድ ነፃ ፍቃዴን እነሆኝ አልኩህ! (እንግዲህ በማማረር ጀምሬ በጸሎት የምፈፅም እጥፍ ባይ ያራዳ ልጅ ሆኜያለሁ ደግሞ አትርሱ ጥንታዊው እርድና ከተቆረቆረበት ከደጃች ዉቤ ወዲህ ጥግ ጥጉን ዶሮ ማነቂያ ነው አልጋ ማለቴ መደብ የያዝኩት ቂ ቂ ቂ)
ተፃፈ እንደኔ ያምላክን ህልውና ለሚፈልጉት ነገር ግን ለጠፋባቸው በተለይ ኦሾአዊያንና ራምፓዊያን ሁሉ
ሃሙስ፣ ማርች 18 ቀን 2010 / 5:13 ኤ ኤም

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on March 20, 2013
  • By:
  • Last Modified: March 20, 2013 @ 4:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With: , ,

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar